ጆርጅ ማይክል አረፈ | ባህል | DW | 27.12.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ጆርጅ ማይክል አረፈ

እንጊሊዛዊዉ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ጆርጅ ማይክል ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰማ። የ 53 ዓመቱ ብሪታንያዊ ሙዚቀኛ መኖርያ ቤቱ ዉስጥ መሞቱ ነዉ የተዘገበዉ። ምዕራባዉያኑ የገናን በዓልን በሚያከብሩበት ዕለት ታኅሳስ 25 ስለ እዉቁ ሙዚቀኛ  ጆርጅ ማይክል ይፋ በሆነዉ ጋዜጣዊ መግለጫ

«ተወዳጁን ልጅ፤ ወንድም እንዲሁም ጓደኛ ጆርጅ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ስናረጋገጥ በታላቅ ኃዘን ነዉ።» ታዋቂዉ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ በምን ምክንያት እንደሞተ በግልፅና በዝርዝር የተነገረ ነገር ግን የለም። አሟሟቱን «ያልተብራራ ግን የማያጠራጥር» ያለው ፖሊስ አስከሬኑ እንደሚመረመር አስታውቋል።
በ1980ዎቹ ወደ ሙዚቃው ዓለም መድረክ ረግጦ በአጭር ጊዜ እውቅናን ያተረፈው ጆርጅ ማይክል በደቡብ ምስራቅ ብሪታንያ ኦክስፎርድሻየር በሚገኝ መኖሪያ ማረፉ ነዉ የተነገረዉ። 
በሙሉ ስሙ ጆርጂስ ካያሪኮስ ፓናጊዮቱ ተብሎ የሚታወቀው ጆርጅ ማይክል፤ በፖፕ ሮክ የሙዚቃ ስልት ላለፉት 30 ዓመታት በማቀንቀኑ ይታወቃል፡፡ ከአራት ዓመት ግድም በፊት ጆርጅ ማይክል በሳምባ ምች ሕመም ይሰቃይ እንደነበርና ለሕይወቱ ያሰጋዋል ነገርግን በማገገም ላይ ነዉ የሚል ዘገባ ወጥቶ እንደነበር ይታወሳል። ቀደም ብሎ ስለ ጆርጅ ማይክል በወጡ ዘገቦች ሙዚቀኛዉ የእዕ ሱስ እንዳለበት ያመላክታሉ። 100 ሚሊየን በላይ የሙዚቃ አልብም ቅጂዎችን መሸጡ የሚነገርለት  ጆርጅ ማይክል በ1977 ኢትዮጵያ በረሃብ ችግር ውስጥ በነበረችበት ወቅት ከሙዚቀኛ ቦብ ጊልዶፍና ሌሎች ሙዚቀኞች ጋር በመሆን በገቢ ማሰባሰባሰብያ የሙዚቃ መድረክ የተሳተፈም ነዉ። ኢትዮጵያዉያን ጨምሮ በዓለም የሙዚቃ አፍቃሪዎች ዘንድ ጆርጅ ማይክል « ዌክ ሚ አፕ ቢፎር ዩ ጎ ጎ » እና « ላስት ክሪስመስ» በተባሉት ሙዚቃዎቹ ታዋቂነትና ተወዳጅትን አትርፎአል።  

አዜብ ታደሰ