ጀርመንና ዘረኝነት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 22.06.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ጀርመንና ዘረኝነት

ጀርመን ውስጥ ዘረኝነት ፣ በዘር ላይ የተመሰረተ አድልዎ እና የውጭ ዜጎች ጥላቻ የሚገኝበትን ሁኔታ የዛሬ ዓመት በተለያዩ ከተሞች ተዘዋውረው የተመለከቱት የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ልዩ አጥኚ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ጄኔቭ ስዊትዘርላንድ ውስጥ የጥናታቸውን ውጤት ይፋ አድርገዋል ።

default

ጊቱ ምዊጋይ

ልዩ አጥኚው ጊቱ ምዊጋይ እ.ጎ.አ ከ ሰኔ 22 እስከ ሐምሌ 1 ,2009 ዓም ድረስ የፌደራል ክፍለ ሐገራትና የማዘጋጃ ቤቶች ባለስልጣናትን ህግ አውጭዎችን እና ህግ አስፈፃሚዎችን ሰፊ ጊዜ ወስደው አነጋግረዋል ። በጀርመን ዘረኝነትን እና የውጭ ዜጎች የሚደርስባቸውን ጥላቻ ለማስወገድ የሚታገሉ የሲቪል ማሕበራት ፣ የአናሳ ነዋሪዎች ፣ የሀይማኖት ቡድናት ተወካዮችን እንዲሁም ከዘረኝነት እና ከዘር አድልዎ እና ከውጭ ዜጎች ጥላቻና ተያያዥ ችግሮች ሰለባዎች ጋርም ሀሳብ ተለዋውጠዋል ። ልዩ አጥኚው ሳምንት ጄኔቭ ውስጥ ባቀረቡት ባለ ሀያ ሁለት ገፅ የጥናት ዘገባ ከዘረኝነት ጋር የተያያዘ አድልዎችን ለመከላከል ጀርመን በቂ ዕርምጃ አለመውሰዷን አስታውቀዋል ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ