ጀርመናውያንና ሳይንሳዊ ያልሆኑ ባህላዊ እምነቶቻቸው፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 12.05.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

ጀርመናውያንና ሳይንሳዊ ያልሆኑ ባህላዊ እምነቶቻቸው፣

አፍሪቃዊ፣ እስያዊ፣ አውሮፓዊም ሆነ አሜሪካዊ፣ የሰው ልጅ በአጠቃላይ፣ ሳይንሳዊ መረጃ የሌላቸውን ልማዳዊ እምነቶች የሙጥኝ የሚለው፣ ተፈጥሮው፣ የፍርሃት ተገዥ ስላደረገው ሳይሆን አልቀረም።

default

በጀርመንና በሌሎችም አገሮች ገደ-ቢስ የሚሰኘው ቁጥር፣ 13

ሰው፣ በተለይ ለማያውቀው፣ ተመራምሮም ገና ምላሹን ላላገኘለት ጉዳይ፣ የራሱን ግምትም ሆነ መላ-ምት በማስቀመጥ፣ አመክንዮ በሌላቸው የተለያዩ ልማዳዊ እምነቶችን የመቀበል አዝማሚያ ይታይበታል።

አስማት፣ ጥንቆላ፣ ሳይንሳዊ መረጃ የሌለው እምነት ፣ እነዚህ ሁሉ፣ እስከዛሬ ድረስ በዕለት-ተዕለት ባህላዊ እንቅሥቃሤ ቦታ አላጡም። ሰይጣን፣ ርኩሳን መናፍስት፣ መላእክትና ተረታዊ ታሪኮች፣ የሰው፣ የማይወገዱ የባህሉ አካላት ሆነው ቀጥለዋል። መጥፎም ሆነ ጥሩ ገድ፣ በሚባሉ ምልክቶች የማመኑና የመጠራጠሩ አባዜ ፣ የሥነ-ልቡና ጠበብት እንደሚሉት፣ የሰው ልጅ ያለመርካት ውጤት ሲሆን፣ ይህ ራሱ ከራሱ፣ ከሰው ፍጥረትና አብሮ ከመኖር ባህል ጋር ተሣሥረው የዘለቁ ናቸው።

ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ፣