ድሬደዋ የቆሻሻ ስፍራን ወደመናፈሻ | ጤና እና አካባቢ | DW | 24.05.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ድሬደዋ የቆሻሻ ስፍራን ወደመናፈሻ

የድሬደዋ አስተዳደር ከሰማንያ ዓመታት በላይ ደረቅ የቆሻሻ መጣያ የነበረዉን ስፍራ ወደመናፈሻነት ሊቀይር መሆኑን ወኪላችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ከስፍራዉ በላከልን ዘገባ አመልክቷል። ሂደቱ ለአካባቢዉ ፅዳትን ብሎም ልምላሜን እንደሚያጎናፅፍ

default

ይጠበቃል። ቆሻሻዉ የልጆቻቸዉ ህይወት ለአደጋ ማጋለጡን ያመለከቱ የአካባቢዉ ኗሪዎች ለዉጡ እንዳስደሰታቸዉ በመግለፅ፤ አያይዘዉም የንፁህ ዉሃ አቅርቦት ችግራቸዉም እንዲፈታላቸዉ ጠይቀዋል። የድሬደዋ አስተዳደር የወሰደዉ እንዲህ ያለዉ ርምጃ የአካባቢ ተፈጥሮን ከመጠበቅ እና ከመከባከብ በተጨማሪ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ተህዋሲያን እንዳይራቡ መንገድ መዝጊያም ነዉ። 

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic