ደቡብ ሱዳንና ሽምግልናው | አፍሪቃ | DW | 06.01.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ደቡብ ሱዳንና ሽምግልናው

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ትናንት አዲስ አበባ ዉስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያካሄዱትን የፊት ለፊት የሰላም ድርድር ዛሬም መቀጠላቸውን የቀድሞዉን ምክትል ፕሬዝዳት ሪክ ማቸርን የሚደግፉት ወገኖች ቃል አቀባይ ዮሐንስ ፑክ አስታወቁ።

Gespräche über Waffenruhe in Südsudan Verhandlungen in Addis Abeba Taban Deng Gai

የደቡብ ሱዳን መንግሥት ተደራዳሪ ቡድን መሪ ታባን ዴን ጋይ

ተደራዳሪዎች በአሁኑ ጊዜ የወደፊቱን ድርድር አጀንዳ በመቅረጽ ላይ መሆናቸውን አደራዳሪዎች ገልጸዋል። ተቀናቃኞቹ ወገኖች እስካሁን የድርድሩ ቀዳሚ ዓላማ በሆኑት እና ሦስት ሳምንት ያስቆጠረውን ጦርነት ማስቆም እና የቀድሞዉ ምክትል ፕሬዚደን የሪክ ማቸር ደጋፊዎች ተወካዮች የደቡብ ሱዳን መንግሥት ያሰራባቸውን 11 አባላቱን ለማስፈታት ላቀረቡት ጥያቄ መፍትሔ ማስገኘት በሚያስችሉት ዋነኛ ጉዳዮች ላይ ገና መደራደር አለመጀመራቸውን ባለሥልጣናቱ አክለው አስረድተዋል።

Gespräche über Waffenruhe in Südsudan Verhandlungen in Addis Abeba Nhil Deng Nhil

የተቃዋሚው ቡድን ተወካይ ኒል ዴንግ ኒል

የሱዳን ፕሬዚደንት ኦማር ሀሰን ኤል በሺር በደቡብ ሱዳን ስለቀጠለው ደም አፋሳሹ ውዝግብ ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ሳልቫ ኪር ጋ ለመምከር ዛሬ ወደ መዲና ጁባ ተጓዙ። የቀድሞዉ ምክትል ፕሬዝዳት የሪክ ማቸር ደጋፊዎች ካለፈው ታህሳስ ወዲh በርካታ ከተሞችን በቁጥጥራቸው ያስገቡ ሲሆን፣በተመድ ግምት መሠረት፣ ሪክ ማቸር ደጋፊዎች እና በፕሬዝዳት ሳልቫ ኪር መንግሥት ጦር መካከል የቀጠለው ጦርነት በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብን አፈናቅሎዋል።

ደቡብ ሱዳን ጋ ግዙፍ የነዳጅ ዘይት ንግድ ግንኙነት ያላት ቻይና በዚችው ሀገር የሚፋለሙት ተቀናቃኝ ወገኖች የኃይሉን ተግባር ባስቸኳይ እንዲያበቁ እና የተኩስ አቁም ደንብ እንዲደርሱ ጥሪ አሰምታለች።

በኢትዮጵያ ጉብኝት የጀመሩት የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋንግ ዪ እንዳስታወቁት፣ ተፋላሚዎቹ ወገኖች በደቡብ ሱዳን ካለፉት ሦስት ሳምንታት ወዲህ የቀጠለውን እና በይፋ ከ1,000 የሚበልጥ ሰው ሕይወት አጥፍቶዋል የሚባለውን ጦርነት የሚያበቁበትን መንገድ ለማስገኘት ቻይና ጥረት በማድረግ ላይ ናት። የደቡብ ሱዳን መንግሥት በጦርነቱ የተነሳ የነዳጅ ዘይቱን ምርት በአንድ አምስተኛ መቀነስ ተገዶዋል።

በእርስ በርስ ውጊያ ላይ የሚገኙትን የደቡብ ሱዳንን መንግሥትና በቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ሪኤክ ማቻር የሚመሩትን ተቀናቃኝ ወገኖች ለመሸምገል አዲስ አበባ ውስጥ ሰሞኑን ጥረት ሲደረግ ነው የሰነበተው፤ ሁለቱን ወገኖች ፊት ለፊት አገናኝቶ እንዲደራደሩ ለማድረግ አድካሚ ሁኔታ ያጋጠመ ቢመስልም፤ ረዘም ያለ ጊዜ ይወስድ እንጂ ሽምግልናው መሥመሩ እንደማይቀር ብሩኅ ተስፋ አለ ተብሏል ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic