ደም የተቀላቀለበት አይነምድር ምንነት | ጤና እና አካባቢ | DW | 10.10.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ደም የተቀላቀለበት አይነምድር ምንነት

የአንድ ሰዉ ጤና በልዩ ልዩ ምክንያቶች ሊታወክ እንደሚችል ሁሉ በሰዉነቱ የተከሰተዉ የጤና እክል የሚገለፅበት መንገድም ይለያያል። ትኩሳት፣ የራስ ምታት እና የመሳሰሉት የዉስጥ ደዌ አይነተኛ ምልክቶች በመሆን ይታወቃሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:39
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:39 ደቂቃ

ደም መታየቱ በራሱ በሽታ ሳይሆን ምልክት ነዉ፤

ከአይነምድር ጋር ደም ተቀላቅሎ የሚወጣበት አጋጣሚም ይኖራል። ከአይነምድር ወይም ከሰገራ የሚወጣዉ የደም አይነት ቀለሙም እንደመንስኤዉ ምንነት እንዲሁ ሊለያይ ይችላል።

በተለያዩ የሰዉነት ክፍሎች ላይ ደም የማየት ነገር ሊያጋጥም ቢችልም በተለይ ግን ከአይነምድር ላይ የሚታየዉ ደም መንስኤም ሊለያይ ስለሚችል ጊዜ ሳይሰጡ በሀኪም መታየቱ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ነዉ የዉስጥ ደዌ ከፍተና ሀኪም ዶክተር ቶሌራ ወልደየስ የመከሩት። አያይዘዉም በፊንጢጣም ከፍተኛ የደም ፍሰት የሚያጋጥም ከሆነ በቀላል ሳይሆን በቀዶ ህክምና ሊረዳ የሚገባዉ ለሀኪሞችም አስቸጋሪ ሊኖር እንደሚችልም አመልክተዋል። ከዚህም ሌላ የዉስጥ ደዌ ከፍተኛ ሀኪም የሆኑት ዶክተር ቶሌራ እንደሚሉት በእንዲህ ያለ ሁኔታ የሚታየዉ ደም በራሱ በሽታ ሳይሆን የበሸታ ምልክት ነዉ። ዋናዉ ነገር ወደሀኪም ዘንድ ሄዶ ተገቢዉን ምርመራ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ መሆኑንም አፅንኦት ሰጥተዋል። ዝርዝር ማብራሪያዉን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

 

Audios and videos on the topic