1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ዩናይትድ ስቴትስ ጦር ጥቃት በሶማሊያ

አሸባብ የሟቾቹን ደም ለመበቀል ዝቷል።

default

የአል ሸባብ ተዋጊ

የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ጦር ሶማሊያ ዉስጥ ተሸሸጎ የነበረ አንድ የአል-ቃኢዳ ተጠርጣሪ አሽባሪና ተባባሪዎቹን ገደለ።የአሜሪካና የሶማሊያ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት በርካታ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሔሊኮብተሮች ደቡባዊ ሶማሊያን ወርረዉ ዋነኛዉን ተጠርጣሪ ጨምሮ በመኪና ይጓዙ የነበሩ አራት የዉጪ ሐገር ሰዎችን ገድለዋል።የሃያ ስምንት አመቱ ኬንያዊ ወጣት አሊ ሳሌሕ ናብሐን ከስድስት አመት በፊት አንድ የኬንያ ሆቴልን ያጋየዉን ቦምብ የሰራና ጥቃቱን ያቀነባበረ ነዉ-ተብሎ ይጠረጠር ነበር።የሶማሊያ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ናብሐንና ተባባሪዎቹ ሶማሊያ ዉስጥ አል-ሽባብን ደግፈዉ ይዋጉ ነበር።አሸባብ የሟቾቹን ደም ለመበቀል ዝቷል።ጌታቸዉ ተድላ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ጌታቸዉ ተድላ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic