የፕሬስ ነፃነት ማሽቶልቆል | ዓለም | DW | 20.04.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የፕሬስ ነፃነት ማሽቶልቆል

ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን የ180 ሃገራትን የፕሬስ ነጻነት ደረጃ በዘረዘረበት ዘገባው እንደጠቆመው የፕሬስ ነፃነት በ2015 በተለይ በአውሮጳ ህብረትና በባልካን ሃገራት ባልተጠበቀ ሁኔታ በእጅጉ ተገድቧል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:35

የፕሬስ ነፃነት ማሽቶልቆልበጎርጎሮሳዊው 2015 በዓለም ዙሪያ የፕሬስ ነፃነት ማሽቆልቆሉን ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች የተባለው የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት አስታወቀ ። ድርጅቱ እንዳለው ባለፈው ዓመት ነፃ መረጃን በሚያስተላልፉ ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በሁሉም አካባቢዎች ጨምሯል ።ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን የ180 ሃገራትን የፕሬስ ነጻነት ደረጃ በዘረዘረበት ዘገባው እንደጠቆመው የፕሬስ ነፃነት በ2015 በተለይ በአውሮጳ ህብረትና በባልካን ሃገራት ባልተጠበቀ ሁኔታ በእጅጉ ተገድቧል ።በድርጅቱ መዘርዝር የፕሬስ ነጻነት ደረጃቸው ከቀነሰው የአውሮጳ ሃገራት መካከል አንዷ ጀርመን ናት ። ስለ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን የ2015 ዓመታዊ ዘገባና ጀርመን ስለተሰጣት ደረጃ የበርሊኑን ወኪላችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic