የፍልስጤም የነፃነት ጥያቄ፤የእስራኤልና የአሜሪካ ተቃዉሞ | ዓለም | DW | 23.09.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የፍልስጤም የነፃነት ጥያቄ፤የእስራኤልና የአሜሪካ ተቃዉሞ

አባስ ንግግር ለማድረግ ወደ አዳራሽ ከመግባታቸዉ በፊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለፍልስጤም ሙሉ የመንግሥትነት እዉቅና እንዲሰጥ መስተዳድራቸዉ የጠየቀበትን ደብዳቤ ለድርጅቱ ዋና ፀሐፊ ለባን ኪ ሙን አቅርበዋል

default

አባስ ማመልከቻዉን ለባን ሲሰጡ

የፍልስጤም የነፃ መንግሥትነት ጥያቄ፥ የእስራኤልና የዋሽንግተን ተቃዉሞ-ቀደም ሲል እንዳልኩት የዛሬዉን የዜና መፅሔት የተካዉ አጭር ዉይይት ርዕሳችን ነዉ።የዋሽንግተን፥ የጂዳና የሐይፋ ወኪሎቻችችን ማለት፥ አበበ ፈለቀ፥ ነቢዩ ሲራክና ግርማዉ አሻግሬ መስመር ላይ ናቸዉ።

የቀድሞዉ የፍልስጤም መሪ ሊቀመንበር ያሲር አረፋት እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር መስከረም 1974 ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ካደረጉት ታሪካዊ ንግግር ወዲሕ ፍልስጤሞች እዉቅና በመጠየቅ ንግግር ሲያደርጉ ማሕሙድ አባስ ዛሬ የሚያደርጉት የመጀመሪያዉ ነዉ።በተያዘዉ እቅድ መሠረት የኛ ስርጭት እንደተጀመረ ነዉ-ንግግር የጀመሩት።

አባስ ንግግር ለማድረግ ወደ አዳራሽ ከመግባታቸዉ በፊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለፍልስጤም ሙሉ የመንግሥትነት እዉቅና እንዲሰጥ መስተዳድራቸዉ የጠየቀበትን ደብዳቤ ለድርጅቱ ዋና ፀሐፊ ለባን ኪ ሙን አቅርበዋል።ፍልስጤሞች ይሕንን ዕለት በታላቅ ድግስ ለማክበር ተሰናድተዋል።የአንዳድ የአረብ ሐገራት ዜጎችም ከፍልስጤሞች ጎን መቆማቸዉን እያረጋገጡ ነዉ።ነብዩ ካንተ ልጀምር፥-ምን ይመስላል የተራዉ ፍልስጤማዊ ወይም የአረቦች ስሜት።

የፍልስጤሞችን ነፃነት የሚትቃወሙት እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ ባንፃሩ የብቀላ እርምጃ ይወሰድብናል በሚል ሥጋት ጉዳዩን በጥንቃቄ እየተከታተሉት ነዉ።ዩናይትድ ስቴትስ በተለይ ግብፅ፥ ሊባኖይና ዮርዳኖስ ያሉ ዜጎችዋ ፍልስጤሞች በብዛት ወደ ሚኖሩበት አካባቢ እንዳይሄዱ መክራለች።እስራኤል ደግሞ በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ፀጥታ አስከባሪዎች በየሥፍራዉ አስፍራለች።

ግርማዉ: እስኪ ባጭሩ ንግረን እዚያ ሥላየሕና ሥለሰማኸዉ የጥንቃቄ እርምጃ።

ግርማዉ በዚሁ ቀጥልልኝ እስራኤል ዲሞክራሲያዊት ሐገር ናት፥ ጠንካራ ጦር ሐይል ያላት ሐብታም ሐገር ናት ለምንድነዉ የሕዝብ ነፃነትን የምትቃወመዉ።እስከ መቼ ነዉ-የፍልስጤሞችን ይሁን ሶሪያና ሊባኖስን ግዛት በሐይል እንደያዘች መቀጠል የምትፈልገዉ።እስኪ የእስራኤል ፖለቲከኞ፥ የፖለቲካ አዋቂዎች፥ ሙሕራንና ጋዜጠኞች የሚሉትን ጠቅለል አድርገሕ ንገረን።

ፍልስጤሞች የነፃ መንግሥትነት እዉቅና ለማግኘት ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ አጥብቀዉ እየተቃወሙት ነዉ።ሁለቱ መንግሥታት የፍልስጤሞች ነፃነት የሚገኘዉ በድርድር ብቻ ነዉ ባይ ናቸዉ።ፍልስጤሞች ግን በዩናይትድ ስቴትስ ሸምጋይነት ላለፉት ሐያ አመታት የተደረገዉ ድርድር ለፍልስጤሞች ያመጣዉ ለዉጥ የለም ነዉ-የሚሉት።

Netanjahu / Ban Ki Moon / UN

ኔታንያሁና ባን

የፍልስጤም-እስራኤሎች ግጭት ዉዝግብ፥ የሚቆመዉ፥ የፍልስጤሞች ነፃነት የሚረጋገጠዉም እስራኤል በሐይል የያዘችዉን የፍልስጤሞች ግዛት ለቅቃ ስትወጣ ነዉ ባዮች ናቸዉ። ዩናይትድ ስቴትስ ግን አልፋ ተርፋ የፍልስጤሞች የነፃነት ጥያቄ ለፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ከቀረበ ድምፅን በድምፅ በመሻር ሥልጣንዋ ዉድቅ ለማድረግ ዝታለች።

አበበ፥- እንደምናስታዉሰዉ ፕሬዝዳት ኦባማ የፕሬዝዳትነቱን ሥልጣን እንደያዙ መጀመሪያ ካደረጓቸዉ ሰወስት ነገሮች የፍልስጤምና የእስራኤልን ድርድር ለማስቀጠል ልዩ መልዕክተኛ መሾም ነዉ።በሁለት ሺሕ ዘጠኝ ካይሮ ድረስ ሔደዉ ባደረጉት ንግግርም ፍልስጤሞች ከስልሳ ዘመን በላይ በዉጪ አገዛዝ ሥር መቆየታቸዉ መቆም አለበት ብለዉ ነበር።አሁን ድርድር፥ ድርድር የሚሉት ኦባማና ሹማምንቶቻቸዉ ለድርድሩ እንቅፋት የሆነዉ እስራኤል በሐይል በያዘችዉ የፍልስጤም ግዛት የአየሁድ ሠፈራ መንደር በማስገንባቷ እንደሆነ ያዉቁታል።ለምንድ አሜሪካኖች እነሱ ያልቻሉትን ድርድር ፍልስጤሞች መቀጠል አለባቸዉ የሚሉት።የነፃነት ጥያቄዉን ምልክታዊ (Sybolic) ቢሆንም ነፃነት መጠየቃቸዉን ዋሽንግተኖች የሚቃወሙት።

Obama UN hoch

ኦባማ

ነብዩ፥ እንደተከታተል ነዉ አረቦች ለፍልስጤሞች የነፃ መንግሥትነት ጥያቄ ሙሉ ድጋፍ ሠጥተዋል።ይሁንና ባለፉት ሃያ ዓመታት በተደረገዉ ድርድር ግን የአረቦች ሚና ምንም ወይም ትንሽ ነበር።እርግጥ ነዉ በማደራድሩ ሒደት አረቦች ቀርቶ ኳርቴት የሚባለዉ ስብስብ ከሚያካትታቸዉ ከዩናይትድ ስቴትስ በስተቀር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፥ የአዉሮጳ ሕብረትና ሩሲያ የጎላ ሚና የላቸዉም ነበር።ግን ረቦች እንደ ባለጉዳይም መከታተል ነበረባቸዉ።አሁን የአሜሪካኖችና የእስራኤል ጠንካራ ተቃዉሞ ባለበት ለፍልስጤሞች የመንግሥትነት እዉቅና ሙሉ ድጋፍ መስጠታቸዉ ምን አስበዉ ነዉ?ምንስ ይጠብቃሉ።

አበበ፥ የዩናይትድ ስቴትስ በአረቦች ዓለም በተልምዶ የሚታወቀዉ ነዳጅ ዘይት ብቻ ሳይሆን ብዙ ሥልታዊ፥ ፖለቲካዊ ጥቅም አላት የኢራቅ ወረራ፥ የሊቢያ ድብደባ፥ አፍቃኒስታን፥ ፓኪስታን ሌሎችም ሥፍራዎች አሁን የፍልስጤምን ጥያቄ ባደባባይ ተቃዉማ የወደፊት ግንኙነቷ እንዴት ይሆናል ተብሎ ነዉ-የሚታሰበዉ።

ነብዩ ሲራክ

አበበ ፈለቀ

ግርማዉ አሻግሬ

ነጋሽ መሀመድ


Audios and videos on the topic