በ13ኛ ወር ጳጉሜ የመንግሥት ተቀጣሪዎች ደሞዝ አለመከፈላቸዉ ካለው የኑሮ ውድነት ጋር ሲታይ ችግር እንደፈጠረባቸው ቅሬታቸውን ለዶይቸ ቬለ የገለጹ አሉ ።
ሌሎች ደግሞ ደሞዝ መከፈሉ ቢቀር እንኳ ለሀገር የአምስትና በየአራት ዓመቱ ደግሞ የስድስት ቀን ነፃ አገልግሎት መስጠታቸዉ በመንግሥት በኩል እውቅና እንዲያገኝ ጠይቀዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ
በኢትዮጵያ ያሉ ስጋ ቤቶች ከሚታወቁበት የልኳንዳ ብቻ አገልግሎት ተላቅቀው እንደ ምግብ ቤት ማገልገል ከጀመሩ ቆይተዋል፡፡ ከዘመኑ ጋር ለመራመድ ጥረት የሚያደርጉ ስጋ ቤቶች ደግሞ ስማቸው ከሚጠራ የመዝናኛ ስፍራዎች መካከል ራሳቸውን ማሰለፍ ችለዋል፡፡ ጥቂቶቹ መሰረታቸውን ከጣሉበት ከተማ ተሻግረው በአዲስ አበባ ቅርንጫፎች እስከ መክፈት ተጉዘዋል፡፡
የብሪታንያ ጦር እንደ ጎርጎሪያኑ1868 ኢትዮጵያ በወረረበት ወቅት ከኢትዮጵያ የዘረፋቸዉ በርካታ ጥንታዊ ቅርሶች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ተዘንግተዉ ነበር። አሁን ግን ትኩረት በመሳባቸዉ ዉዝግብ አስከትለዋል። እነዚህን የሚቆጣጠሩት ተቋማት ቅርሶችን እንደያዙ በማቆየትና ለጎብኚዎች ማሳያታቸዉን በቀጠሉ ኃላፊነት አጣብቂኝ ዉስጥ ገብተዋል።
አፄ ቴዎድሮስ ሃገሬ በጠላት እጅ አትወድቅም ብለዉ ራሳቸዉን ከሰዉ በኋላ በ1868 ዓ.ም ከመቅደላ አምባ የተዘረፉት ቅርሶች በተለይ ከ500 በላይ የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶች ያሉባቸዉ የብራና ጽሑፎች፤ ፤ የንጉሣውያን የወርቅ ዘውዶችና ጌጣ ጌጦች፣ እንዲሁም ወደ አስር የሚሆን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ታቦታት በእንግሊዝ የተለያዩ ሙዚየሞች ይገኛሉ።