የጨፌ ኦሮሚያ አስቸኳይ ስብሰባ | ኢትዮጵያ | DW | 25.10.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጨፌ ኦሮሚያ አስቸኳይ ስብሰባ

ጨፌ ኦሮሚያ ባካሄደዉ አስቸኳይ ስብሰባ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አስመልክቶ ባካሄደዉ ዉይይት «ህዝብን ወክለዉ» በምክር ቤቱ ዉስጥ ያሉት የአዋጁን አስፈላጊነትና አፈፃጸሙን ለኅብረተሰቡ የተጠናከረ ሃሳብ ማስጨበጫ መስጠት እንደሚያስፈልግ፤ ችግር ሲፈጠርም በአስቸኳይ የሚፈታበትን መንገድ መፈለግ አለባቸዉ የሚለዉ ላይም ማተኮሩን ለመረዳት ተችለዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:59

ጨፌ ኦሮሚያ

ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች አአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መንግሥት እንደሚለዉ ነገሮችን «እያረጋጋ» ሳይሆን ኅብረተሰቡን «ለፍራትና ስጋት» ዳርጎታል ይላሉ። አዋጁ ከታወጀ በኋላ የእስከ ዛሬ አፈፃፀሙን አስመልክቶ ምክር ቤቱ ገምግሞ ተወያይቶበት ይሆን ብለን በጨፌ ኦሮምያ ጽሕፈት ቤት በምክትል የቢሮ ኃላፊ ደረጃ የኮሙኒኬሼንና የመረጃ አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት የሆኑት አቶ ሀብታሙ ደምሴ ጠይቀን ነበር፣ «የአዋጁን አስፈፃሚነና የሚፈፀምባቸዉን ቦታዎች መለየት የተጀመረዉ አሁን ስለሆነ በተጨባጭ መሬት ላይ ያለዉ ላይኖር ስለሚችል ለግምገማ አለበቃም። አዋጁን መፈፀም የተጀመረባቸዉ ቦታዎች ላይ ያለዉን ሁኔታ ጨፌ አንስቷል፣ እጥረት ሊኖር ይችላል፣ ሰዎችን በማያሰፈልግ አኳኋን ሊጎዳ ይችላል የሚለዉ ፍራቻ ላይ ለተነሱት ጥያቄዎች መልስ ተሰጥቷል።»


ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉት የአዳማ ነዋሪ ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተሉ እንደነበር ተናግረዉ ጨፌ አስቸኳይ ስብሰባ የጠራዉ አዋጁን ለማፅደቅ አቅዶ እንደነበረ እና ሳይፀድቅ በፊትም «በህዝብ ተመረጡ ወይም ህዝብን ወክለዋል» የተባሉት በደምብ ይወያዩበታል ተብሎ ቢጠበቅም፤ ይህ ግን ሳይደረግ ቀርቶ ዝም ተብሎ እንዲያልፍ ተደርጓል ይላሉ።


እሁድ ዕለት ደግሞ የቀድሞ የጨፌ ምክር ቤት አፈ ጉባዬ የነበሩት አቶ ለማ መገርሳ ከስልጣናቸዉ ተነስተዉ አቶ እሸቱ ዳሴ በምትካቸዉ ተሹመዋል። አቶ ለማ ደግሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ አቶ ኡመር ሁሴን፤ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ተደርገዉ መሾማቸዉን አቶ ሀብታሙ ይናገራሉ። ይህን ጨምሮ አራት ሰዉ በምክር ቤቱ ዉስጥ ለዉጥ ሲደረግ፤ ቀሪዉ 13 ሰዉ ደግሞ እንደ አዲስ ለምክር ቤቱ ካቢኔ አባላት መመረጣቸዉንም ያስረዳሉ። ከምክር ቤቱም ዉጭ ለኦሮሚያ ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ወሮ ኂሩት ብራሳ፣ ለኦሮሚያ ረድዮና ቴሌቪዥ ተቋም አቶ ጌቱ ወዬሳና አቶ ኤልማ ቃጴ ደግሞ ለክልሉ ዋና ኦዲተርነት ተሹመዋል።

ይህ ሹም ሽር አሁን ለምን አሰፈለገ? ለሚለዉ አቶ ሀብታሙ፣ «አሁን መንግሥት ያለበትን ሁኔታ ይረዳሉ ብዬ አስባለዉ። የማህበረሰቡ ጥያቄዎች በተለያዩ ጊዜያት ሲነሱ ነበር። የመልካም አስተዳደር፣ የልማት ጥያቄና ሥራ አጥነትን የተመለከቱ ጥያቄዎች ተነስተዋል። ለዚህም መልስ ለመስጠት በተደረገዉ ሙከራ የተፈለገዉን ፍላጎት ማሟላት ላይ እጥረት ስለነበረዉ፣ ይህን ለመፍታት ሹም ሽሩ ተደርጓል።»

በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ በፌስ ቡክ ገፃችን እንዲወያዩ ከጋበዝናቸዉ ዉስጥ አንዳንዶች አዋጁ ተፈፃሚ በመሆኑ ህዝቡ «እፎይታ» አግኝቷል ሲሉ ሌሎች ደግሞ «ጉልቻ ቢቀየር ወጥ አያጣፍጥም፣ አስተሳሠባቸው ቢለወጥ እንጂ ካድሬ ቢለዋውጡ አይገባንም፣ ዙሮ ዙሮ መዝጊያው ጭራሮ» የሚሉ አስተያየቶችን ሰንዝረዋል።

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሠ 

Audios and videos on the topic