የጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ስንብትና የቀብር ስነ ስርዓት | ኢትዮጵያ | DW | 31.08.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ስንብትና የቀብር ስነ ስርዓት

የአቶ መለስ የቀብር ስነሥርዓት እሑድ በመንበረ ጸባኦት ቅድሥት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን እንደሚፈፀምና የውጭ ሃገራት መሪዎች ንግግርና የስንብቱ ስነ ስርዓት ደግሞ በመስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ዲና ሙፍቲ ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ።

የፊታችን እሁድ ነሐሴ 27 2004 ዓም የቀብር ስነ ስርዓታቸው ለሚፈፀመው ለኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በተለያዩ ደረጃዎች ስንብት እየተካሄደ ነው ። ከትናንት አንስቶም የየማህበረሰቡ ተወካዮች በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ በመገኘት ሻማ ና ጧፍ በማብራት ሃዘናቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው ። በአፍሪቃ ህብረትም ዛሬ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሃዘን መግለጫ ስነ ስርአት ተካሂዷል ። የአቶ መለስ የቀብር ስነሥርዓት እሑድ በመንበረ ጸባኦት ቅድሥት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን እንደሚፈፀምና የውጭ ሃገራት መሪዎች ንግግርና የስንብቱ ስነ  ስርዓት ደግሞ በመስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ዲና ሙፍቲ ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ። ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ አዘጋጅቶታል ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic