የጠበብቶች እጥረት በአፍሪቃ | አፍሪቃ | DW | 30.05.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የጠበብቶች እጥረት በአፍሪቃ

ጥሩ ክፍያ ያለው ስራ ፖርቹጋላውያንን ወደ አንጎላ ሲያስኬድ በሌላ በኩል አፍሪቃ ውስጥ የስራ አጥ ወጣቱ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ እያለ ነው። አፍሪቃ የዜጎቿን እውቀት መጠቀሙ ላይ ችግር የገጠማት ይመስላል። ሰሞኑን የአፍሪቃ ምጣኔ ሀብታዊ

ሳምንት በፍራንክፈርት ጀርመን ተካሂዶ ነበር። አርኑልፍ ክሪስታ የበርካታ አፍሪቃ አገሮች የንግድ ስልት ገብቷቸዋል። BAUER SPEZIALTIEFBAU የተሰኘ የአንድ የህንፃ ተቋራጭና የጀርመን ድርጅት ባልደረባ ናቸው። ድርጅቱ ትላልቅ ህንፃዎች እና ድልድዮችን አፍሪቃ ውስጥ ይሰራል። ድርጅቱ ትርፋማ ሊሆን የቻለው አፍሪቃ ውስጥ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ከፍቶ የአገሪቷን ዜጎች ቀጥሮ በማሰራቱ ነው።ይሁንና መሀንዲስ ክሪስታ ስራቸው እንዲህ ቀላል እንዳልሆነ ነው የሚናገሩት። ድርጅቱ አንድን ሰራተኛ ካሰለጠነ በኋላ ወዲያው ሌላኛው መስሪያ ቤት ይቀማቸዋል።

Brückein Mali *** DW/ Ruth Reichstein CMS: 07.2009

የማሊ ድልድይ

« በአንዳንድ የአፍሪቃ ሃገሮች የተማሩ የሰው ኃይል እጥረት አለ። በዚህም የተነሳ ፉክክር ይታያል። አንጎላ ውስጥ አንዳንድ የመንግስት ድርጅቶች ሊከፍሉት የሚችሉት ብዙ ገንዘብ አላቸው ። ጀርመን ውስጥ አንድ ሰው ስራውን ከቀየረ አምስት ወይንም አስር ከመቶ የደሞዝ ጭማሪ ሊያገኝ ይችላል። ወደ አፍሪቃ ከተክሄደ ግን እጥፍ ወይንም ሶስት እጥፍ ደሞዝ ሊገኝ ይችላል። ያኔ ስራ መቀየርን ተመራጭ ያደርገዋል።»

የአፍሪቃ ምጣኔ ሀብት ለአመታት ያለማቋረጥ ያድጋል። በርካታ የውጭ ባለሀብቶች በዚች ክፍለ ዓለም መዋዕለ ንዋይ ያፈሳሉ። በተለይም በተፈጥሮ ሀብት በታደሉት ሀገሮች! ህዝቡ ከዚህ ትርፋማ እንዲሆን ስልጠና በመስጠት እንተባበራለን ይላሉ አንድሪያስ ኩኒግ። የጀርመን አለም አቀፍ ተራዕዶ ድርጅት በእንግሊዘኛ ምህፃሩ GIZ የትምህርት፣ የሙያና የስራ ዘርፍ ኃላፊ ናቸው። « እጅግ ከፍተኛ ያለ የህብረተሰብ ቁጥር ነው ያለን። ከትምህርት ቤት ወተው በቂ የሙያ ስልጠና የማያገኙ ወይንም አንድ የትምህርት ደረጃ ላይ የማይደርሱ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች አሉን። በሌላ በኩል ደግሞ አፍሪቃ የበቂ የሰው ኃይል እጦት አለባት። ቢያንስ በአሁኑ ጊዜ ምጣኔ ሀብታዊ እድገት በሚታይባቸው ወይንም በአለም አቀፉ ገበያ ላይ ራሳቸውን ማስተዋወቅ በሚፈልጉ የአፍሪቃ አገሮች ላይ! በእንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች የውጭ ዜጎችን ለስራ ማስገባት አስፈላጊ ይሆናል። ይህ ደግሞ ረዘም ላለ ጊዜ አገሪቷን የሚጎዳ እና ውድም ነው የሚሆነው።»

The city of Cape Town as the sun sets and light are switched on in Cape Town, South Africa, Wednesday, Oct 26, 2011. Cape Town won a Designer City Award for 2014 on Wednesday. The award was in recognition of the city's accomplishments in using design as a catalyst for development and reinvention, as well as for improving its social, cultural and economic environments.(ddp images/AP Photo/Schalk van Zuydam)

ደቡብ አፍሪቃ በሌሊት

በአንዳንድ አለም አቀፍ ድርጅቶች ከአገሬው ይልቅ የውጭ ዜጎችን የመቅጠር አዝማሚያ ይታያል። እንደዚህ አይነቱ አሰራር ስኬታማ ሊሆን የሚችለው ግን በትምህርት ላይ ያተኮረ ተጨማሪና ዘላቂ ስራ ሲከናወን ብቻ ነው። ይህ ትኩረት እንዲሰጠው ካሳሰቡት ምሁራን አንዱ ሴኔጋላዊው ሳይንቲስት ቦባካር ቤሪ - የምዕራብ አፍሪቃ የአየር ንብረት ለውጥ ጥናት አስተባባሪ ናቸው። በአፍሪቃ ዮንቨርሲቲ ተተኪ የማፍራት ችግር አለ ይላሉ። ለዚያም ሲሉ ልጆቻቸውን ወደ ውጪ ሀገር መላኩን መርጠዋል። «እውነቱን ለመናገር ልጆቼን ወደ አፍሪቃ ዮንቨርሲዎች ሳይሆን ወደ ሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ ነው የላኳቸው። ምክንያቱም በአፍሪቃ ዮንቨርሲቲዎች ደስተኛ አይደለሁም። የትምህርት አሰጣጣቸው አለም አቀፉ ደረጃን የጠበቀ አይደለም። በቂ የትምህርት ክፍል ፣ በቂ አስተማሪ ወይንም ቤተ ሙከራ የለም። ይህም የትምህርት ጥራቱ ደካማ እንዲሆን ያደርገዋል።»

መሀንዱስ አርኑልፍ ክሪስታ መስራቤታቸው BAUER SPEZIALTIEFBAU ምን ያህል ገንዘብ ለስልጠናና ትምህርት እንደሚያወጣ ሲናገሩ ብዙዎች ይደነግጣሉ ። ለመስሪያ ቤታቸው እውቀት ሀብት ነው። ይሁንና ይላሉ ክሪስታ የሳቸው መሰል ድርጅቶች የአፍሪቃ የትምህርት ችግሮች ብቻቸውን ሊወጡት አይችሉም።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic