የጎምቱው ፖለቲከኛ ኃይሉ ሻውል መታሰቢያ  | ኢትዮጵያ | DW | 17.10.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጎምቱው ፖለቲከኛ ኃይሉ ሻውል መታሰቢያ 

ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት እና ሥርዓተ-ቀብራቸው አዲስ አበባ ላይ የተፈጸመው ኢንጂኔር ኃይሉ ሻውል የፖለቲካ ትግል አጋሮች እና ቤተሰቦቻቸው በሻማ የማብራት ሥነ-ሥርዓት የቀድሞውን ፖለቲከኛ አስበዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:51

የኃይሉ ሻውል መታሰቢያ 

በ1997 ዓ.ም የድኽረ ምርጫ ኩኸት ለእስር ከተዳረጉት እና ኋላ በወቅቱ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከተፈቱ ፖለቲከኞች እና ምሁራን መካከል አንዱ ኃይሉ ሻውል ነበሩ። በ80 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ጎምቱ ፖለቲከኛ በአባይ ሸለቆ ጥናት በማድረግ ይታወቃሉ። ኃይሉ ሻውል የመጀመሪያው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ኃላፊም ነበሩ። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እንዲሁም የቅንጅት ለአንድነት እና ለዴሞክራሲ ፕሬዝዳንት በመሆን ላገለገሉት ኢንጂኔር ኃይሉ ሻውል በተዘጋጀ የመታሰቢያ መሰናዶ ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው የዶይቼ ቬለ ወኪል ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ የሚከተለውን ዘገባ አድርሶናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
እሸቴ በቀለ
ሒሩት መለሰ
 

Audios and videos on the topic