የግብፅ የለውጥ እንቅሥቃሤና ውጤቱ ፣ | እንወያይ | DW | 03.07.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

እንወያይ

የግብፅ የለውጥ እንቅሥቃሤና ውጤቱ ፣

የለውጡ እንቅሥቃሤ፣ የግራ፤ የቀኝ ፤ አብዮታዊ ፣ ወግ አጥባቂ ተብሎ፣ በርእዮት የሚመደብ አልነበረም። ንጉሥ የማይባል ፣ ግን፤ ንጉሥ መሰል ፣ 30 ዓመት በመንበር ላይ የተቀመጠ ፣ የአንድ ሰው ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ አስመርሮት የነበረው

ህዝብ ፤ መሠረታዊ መብቶችን ፤ ነጻነትን፣ ፍትኅንና ርትእን ፣ የሥራ ዕድልን ፤ የኑሮ መሻሻልን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን አንግቦ ነበረ ፣ የተንቀሣቀሰው። የለውጥ ነፋስ ፣ እንደ ሰደድ እሳት ባቀጣጠለው ፣ የለውጥ ዘመቻ፤ በተለይ ወጣቱ ትውልድ፣ በዘመናዊ የማኅበራዊ መገናኛ መሳሪያዎች ረዳትነት፤ በጽናት ታገለ። ታህሪር አደባባይ ፣ ልክ እንደ ስሙ በትክክል የነጻነት አደባባይ፣ መሆን አለበትም አለ። ግፊቱን በማጠናከርና መስዋእትነትም በመክፈል፤ አምባገነኑን መሪ ከሥልጣን አስወገደ። ሆኖም ፤ አስተዳደሩን በሞግዚትነት ከሚቆጣጠረው የጦር ኃይሉ ም/ቤት ተጽእኖ፣ ሥልጣኑን በእርግጥ ፈልቅቆ ለሲቭል አስተዳደር ማስረከብ ተችሏል? የሚቻልስ ነው ወይ? በግብፅ ፣ የአስተዳደር ለውጥ፤--መነሻው፤ ሂደቱና አስተምህሮቱ፤ የዛሬው የውይይት መድረክ ርእሳችን ነው።

ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic