የግብፅ መንግሥት የተቃዉሞ ሰልፈኞችን አሰረ | አፍሪቃ | DW | 16.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የግብፅ መንግሥት የተቃዉሞ ሰልፈኞችን አሰረ

ግብጽ ውስጥ ከ150 በላይ ሰዎች ፍቃድ ያልተሰጠው መንግሥትን የሚቃወም ሰልፍ ላይ በመሳተፍ በሚል ከሁለት እስከ አምስት ዓመታት የሚደርስ የእስር ፍርድ እንደተበየነባቸው በሰፊዉ እየተዘገበ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:42
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:42 ደቂቃ

የግብፅ መንግሥት የተቃዉሞ ሰልፈኞችን አሰረየሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች የግብጽ ፍርድ ቤት በጅምላ ሰዎቹ ላይ የሰጠው ፍርድ አግባብ አይደለም ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። 101 ሰዎች እንደ ጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር በ2013 ጸንቶ የነበረውን የጎዳና ሰልፍ ዕገዳ በመተላለፍ በሚል የአምስት ዓመት እሥር ተበይኖባቸዋል ሲል አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል። የተቀሩት አምሳ አንዱ ደግሞ የሁለት ዓመት እስራት የተፈረደባቸው የግብጽ መንግሥት በቁጥጥሩ ስር የሚገኙ ሁለት የቀይ ባሕር ደሴቶችን ለሣዑዲ ዓረቢያ ለመስጠት መወሰኑን በመቃወም ሰልፍ በመውጣታቸው እንደሆነ ነዉ የተነገረዉ። ስለ ግብፅ ፍርድ ቤት ብይንና ስለ ግብፅ ወቅታዊ ሁኔታ ኬንያ የሚገኘዉ ወኪላችን በስልክ አነጋግረነው ነበር ።

ከፋሲል ግርማ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዩ ለገሠ

Audios and videos on the topic