የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት አመታዊ ዘገባ | ዓለም | DW | 20.10.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት አመታዊ ዘገባ

በያዝነዉ የአዉሮጻዉያኑ 2010 አ.ም በርካታ አፍሪቃዉያን አገሮች ከቅኝ ግዛት የተላቀቁበትን አመት ቢያከብሩም ቅሉ አፍሪቃዉያን ጋዜጠኞች ዛሪም የፕሪስ ነጻነታቸዉን አላገኙም ሲል አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት አመታዊ ዘገባዉን ይፋ አድርጎአል።

default

ድርጅቱ ዛሪ ይፋ ባደረገዉ አመታዊ ዘገባዉ የአፍሪቃዉ ቀንድ አገራት በፕሪስ ነጻነት ረገድ የመጨረሻዉን ደረጃ ይዘዉ እንደሚገኙ እና በተለይ የመካከለኛዉ አፍሪቃ አገራት እና በምስራቅ አፍሪቃ የፕሪስ ነጻነት አሳሳቢ እና አስጊ ሁኔታ ላይ መድረሰኑ ገልጾአል። በዚህ ዘገባ ዙርያ መቀመጫዉን በፈረንሳይ ያደረገዉ ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት የአፍሪቃዉ ክፍል ተጠሪ Ambroise Pierre ን አዜብ ታደሰ አነጋግራ ዘገባ አጠናቅራለች።

አዜብ ታደሰ፣ ተክሌ የኋላ