1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የጉግል ዛቻና ቻይና

ጉግል በዚህ ሳምንት ማክሰኞ በሰጠው መግለጫ በቻይንኛ ቋንቋ በሚያቀርባቸው መረጃዎች ላይ የቻይና መንግስት በሚያካሂደው ቅድመ ምርመራ ና ክትትል ምክንያት ስራውን ሊያቆም እንደሚችል አስጠንቅቋል ። ቻይና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለህዝቡ እንዲደርሱ የማይፈለጉ መረጃዎችን መርምሮ የሚያግድ ትልቅ የኢንተርኔት ግንብ ገንብታለች ።

default

የቁጥጥሩን ሂደት የተመለከቱ ዝርዝር መረጃዎች የመንግስት ሚስጥር ቢሆኑም የቻይና ባለስልጣናት ስራውን እንዴት እንደሚያካሂዱ ግን ይታወቃል አንደኛው መንገድ አንድ መረጃ ሙሉ በመሉ እንዳይተላለፍ ማገድ የሚያስችል ነው ። አንድ የኢንተርኔት ተጠቃሚ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹን ድርጅት የአምነስቲ ኢንተርናሽናልን ድረ ገፅ ለመክፈት ሲሞክር የተሳሳተ ፍለጋ መሆኑን ወይም ድረ ገፁ እንደሌለ የሚጠቁም ውጤት ነው የሚያገኘው ። ሁለተኛው የኢንተርኔት ቅድመ ምርመራ መንገድ ደግሞ ውድ ሲሆን ይህም ተፈላጊው ድረ ገፅ ቶሎ እንዳይገለጥ ማዘግየት የሚያስችል ዘዴ ነው ።

ዮርግ ብሩንስማን ፣ ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ