ጅቡቲና ኤርትራ በድንበር ግዛት ይገባኛል ጥያቄ በሚወዛገቡበት በጋራ ድንበራቸው በሚገኘው የራስ ዱሜራ አካባቢ ካታር አስፍራው የነበረውን ሰላም አስከባሪ ጦሯን ካስወጣች በኋላ በሁለቱ ሀገራት መካከል ውጥረቱ እንዳዲስ ተካርሯል። የካታር ጦር መውጣትን ተከትሎ ኤርትራ ወታደሮቿን በአወዛጋቢው ግዛት አስፍራለች።
ይህም ተገቢ አይደለም ስትል ጅቡቲ ለተመድ እና ለአፍሪቃ ህብረት አቤት ብላለች። ይህንኑ ውዝግብ በተመለከተ ከጅቡቲና ከኤርትራ መረጃ እንደደረሰው ያስታወቀው የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ትናንት በጉዳዩ ላይ መክሮ ሁለቱ ሀገራት ውዝግቡን ከማባባስ እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
መክብብ ሸዋ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ