የጀርመን ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት ፍፃሜ | ኢትዮጵያ | DW | 20.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የጀርመን ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት ፍፃሜ

ጋውክ ጀርመን ለኢትዮጵያ ልማት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምትሰጥ አስታውቀዋል ። ሆኖም በኢትዮጵያ በዲሞክራሲና በሰብአዊ መብት አጠባበቅ ረገድ ብዙ መሰራት ያለባቸው ተግባራት እንዳሉ ተናግረዋል ።

የጀርመን ፕሬዝዳንት ዮአሂም ጋውክ በኢትዮጵያ ያደረጉትን የ 4 ቀናት ጉብኝት ዛሬ አጠናቀዋል ። በ4 ቀናት የኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር የተነጋገሩት ጋውክ ጀርመን ለኢትዮጵያ ልማት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምትሰጥ አስታውቀዋል ። ሆኖም በኢትዮጵያ በዲሞክራሲና በሰብአዊ መብት አጠባበቅ ረገድ ብዙ መሰራት ያለባቸው ተግባራት እንዳሉ ተናግረዋል ። ጋውክ ዛሬ ከአዲስ አበባ ከመነሳታቸው በፊት የአዲስ አበባውን የተግባረ እድ ትምህርት ጎብኝተዋል ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic