የጀርመን እጩ ተፎካካሪዎች ክርክር | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 04.09.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የጀርመን እጩ ተፎካካሪዎች ክርክር

ብዙ የተነገረለት እና የተጠበቀዉ የጀርመን ፖለቲከኞች የቴሌቪዥን የፊት ለፊት ክርክር ትናንት ማምሻዉን ተካሂዷል። ምርጫዎ ሦስት ሳምንታት ሲቀሩት በተካሄደዉ የጀርመን ፖለቲከኞች የቴሌቪዥን ክርክር የስደተኖች ጉዳይ፣ የቱርክ እና የጀርመን ፍጥጫ፣ የዩናይትድ ስቴትስ አዲስ አስተዳደር እና የሰሜን ኮርያ ጉዳይ ዋና መነጋገሪያ ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:56
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:56 ደቂቃ

የሜርክል እና የሹልስ የፊት ለፊት ክርክር፤

አራት አወያዮች በተሰየሙበት ክርስቲያን ዴሞክራቷ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና ሶሻል ዴሞክራቱ ተፎካካሪያቸዉ ማርቲን ሹልስ ያካሄዱት ክርክር ዋናዉ ትኩረቱ የስደተኞች በጀርመን ከኅብረተሰቡ ጋር ተዋህደዉ የመኖራቸዉ ጉዳይ ላይ እንደሚሆን ቢጠበቅም ፖለቲከኞቹ ጉዳዩን እንዳድበሰበሱት ነዉ ተንታኞች የሚናገሩት። ክርክር በኋላ የተሰበሰበ የሕዝብ አስተያየት ምዘና አንጌላ ሜርክል የተሻለ ተወያይ እንደነበሩ መጠቆሙም ተገልጿል። እንዲያም ሆኖ ሸዋዬ ለገሠ ያነጋገረቻቸዉ እዚህ ጀርመን ሀገር የሚኖሩት የሕግ እና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ ክርክሩ ኅብረተሰቡ ከሚፈልገዉ ሀገራዉ ጉዳይ ይልቅ በዉጭ ጉዳይ በመሸፈኑ ብዙም የሕዝቡን ትኩረት መሳብ ተስኖታል ይላሉ።

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች