የጀርመን መራኂተ-መንግሥት ጉብኝት በዩናይትድ እስቴትስ፣ | ዓለም | DW | 03.11.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የጀርመን መራኂተ-መንግሥት ጉብኝት በዩናይትድ እስቴትስ፣

የጀርመን መራኂተ-መንግሥት ወ/ሮ አንጌላ ሜርክል፣ ትናንት ዋሽንግተን በመግባት ከፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን ፣

የጀርመን መራኂተ-መንግሥት ጉብኝት በዩናይትድ እስቴትስ፣

በዛሬው ዕለት በአሜሪካ ም/ቤት ዲስኩር እንደሚያሰሙ ይጠበቃል። እ ጎ አ በ 1957 ዓ ም፣ ያኔ፣ የምዕራብ ጀርመን መራኄ-መንግሥት የነበሩት ኮንራድ አደናዎር በዩናይትድ እስቴትስ ም/ቤት ንግግር ካሰሙ ወዲህ ፣ ከ 42 ዓመታት በኋላ፣ ይኸው ተመሳሳይ ዕድል ያጋጠማቸው የጀርመን መሪ ፣ ወ/ሮ አንጌላ ሜርክል ናቸው። የጀርመን ተጓዳኝ ዩናይትድ እስቴትስ ፣ ከበርሊን አስተዳደር ብዙ ትጠብቃለች።

ይልማ ኃይለ-ሚካኤል/ተክሌ የኋላ/ነጋሽ መሐመድ