የዶይቸ ቬለ መ/ግብር ተከታታዮች | የዶይቸ ቬለ 60ኛ ዓመት | DW | 10.06.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የዶይቸ ቬለ 60ኛ ዓመት

የዶይቸ ቬለ መ/ግብር ተከታታዮች

ዶይቸ ቨለ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥርጭቱን ያሰማው እ ጎ አ ግንቦት 3 ቀን 1953 ዓ ም ነበር። ከ 60 ዓመታት አገልግሎት ወዲህ ዶች ቨለ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል?ሳይቀየር የቀጠለው ምንድን ነው? ተለወጠውስ? 12 ዓመታት ዶቸ ቨለን ለመሩት ለኤሪክ ቤተርማን የቀረቡ ጥያቄዎች ናቸው።

ዋናው ሥራ አስኪያጅ፤ ኤሪክ በተርማን ፣ በተለይ ከሠለስቱ አምዓት መግቢያ ወዲህ በዶቸ ቨለ ላይ ዐቢይ ተጽእኖ ያሳረፈ ጉዳይ ምን እንደሆነ በመግለጽ ሲያብራሩ--መስከረም 1 ቀን 1994 ዓ ም የተፈጸመው ድርጊት ሰፊ ተጽእኖ ማሳደሩ አንድ ትልቅ ክሥተት መሆኑን ያወሳሉ። «ሥራ ከመጀመሬ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ፣ ዶይቸ ቨለ ለሀገራችን ያለውን ትርጉም፣ በራስ ድምፅ መደመጥ ያለውን ከፍተኛ ጠቀሜታ አረጋገጠልኝ። ከዚያ ባሻገር፤ አስደናቂው ፈጣኑ የሥነ ቴክኒክ ዕድገት ነው በዓለም ዙሪያ በመገናኛ ረገድ አብዮታዊ ለውጥ ነው ያስከተለው። ይህም ዝግጅትንና ከመገናኛ ብዙኀን የሚቀርበውን መሰናዶ ማስፋፋትን ይመለከታል። የአጠቃቀሙ ስልትም በእጅጉ ተለውጧል »።


ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ባከተመ በ 8ኛው ዓመት የተቋቋመው ዶቸ ቨለ ተግባሩ፤ የጎደፈው የጀርመን ታሪክ ከተገታ በኋላ፤ አገሪቱ ወደ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የምትቀላቀልበትን መንገድ መጥረግ ነበረ። ታዲያ የ 60 ዓመቱ የ ዶይቸ ቨለ ተግባር እንዴት ይታያል?
«ያኔም ሆነ ዛሬ፣ ዶቸ ቨለ፤ ሃገራችንንና እሴቶቿን ማሳወቅ ይኖርበታል። ዶይቸ ቨለ፣ ጀርመን በአውሮፓዊነት እያደገች የመጣች ባህል ያላት ፤ በነጻነት የተሰናዳ ህገ መንግሥትና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር የገነባች ሀገር መሆኗን ማሳወቅ መመሪያ ነው ይላል እ ጎ አ በ 2005 ዓ ም የወጣው የጣቢያው መመሪያ ደንብ። የዝግጅት መርኀ-ግብራችንን ዘመናዊ ከማድረጉም እንዲስፋፋም አብቅቶታል።


በብዙ ቋንቋዎች በምናቀርባቸው ዝግጅቶችና በአካዳሚአችን፤ በአሁኑ ጊዜ ለባህል ግንኙነት መስክ ሆነናል። እናም ለጀርመናውያንና ለሌሎች አመለካከት መድረክ ነን። እኛ፣ የነጻነትና የሰብአዊ መብት ድምጽ ነን የሚል ግንዛቤ ነው ያለን። ከዚያም ባሻገር የጀርመንና ቋንቋ እንዲስፋፋ እናበረታታለን። ይኸም ከዕለታዊ ተግባራችን አንዱ ነው።»
በ 30 ቋንቋዎች የሚያሠራጨው ዶይቸ ቨለ ፣ ለሥራው መመሪያ የሚያደርገውም ሆነ ዋና ትኩረት የሚሰጠው ለአድማጮቹና ለተመካቾቹ ሲሆን፣ በአጭር ሞገድ የራዲዮ ፕሮግራሞች፤ በሳቴላይት ቴሌቭዥንም ዝግጅቶችን ያሠራጫል። የኢንተርኔት አገልግሎትን ቀደም አድርጎ ነው የጀመረው። እናም በተለያዩ የህዝብ መገናኛ ዘርፎች አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ለመሆን በቅቷል። ከአንድ ዓመታ ገደማ በፊት ጀምሮ ፤ በ 6 የዓለም አካባቢዎች የቴሌቭዥን ዝግጅቶች ይሠራጫሉ። በጀርመንኛ ፤ በእንግሊዝኛ፤ በእስፓኝኛና በዐረብኛ በሌሎች ቋንቋዎችም፤ ለተጓዳኝ ጣቢያዎች የቴሌቭዥን ዝግጅቶችን ያሰናዳል። በኦንላይንም ፣ ኤሪክ በተርማን እንዳስረዱት፣ በአሁኑ ጊዜ በማኅበራዊ ኑሮ መገናኛ ዘዴዎችና በተንቀሳቃሽ ስልኮችም አገልግሎት ይሰጣል።
ዋናው ሥራ አስኪያጅ እንደገለጹት፤ዶይቸ ቨለ ፣ በህግ የሥራ ተልእኮ ያለውና ፣ በመንግሥት በጀት የሚንቀሳቀስ ሆና ሳለ፣ ባለፉት60 ዓመታት በጋዜጠኝነቱ አሠራር ረገድ ነጻ ሆኖ ነው የኖረው።
ባለፉት ዐሠርተ ዓመታት የህዝብን አመኔታ ያተረፈው፣ ዶይቸ ቨለ በአካዳሚው በኩል የሚያቀርበው ፤ በዓለም ዙሪያ ሰፊ ተቀባይነትን አግኝቷል።


ዶቸ ቨለ ፣ በተርማን እንዳብራሩት፤ በዓለም ዙሪያ ነጸነት የሚንጸባርቅበትና ግልጽ የመገናኛ- ብዙኀን ሥርዓት እንዲዘረጋ ሲያሳስብ ከሞላ ጎደል 50 ዓመት ሊሞላው ምንም ያህል አልቀረው። የጀርመን የልማት ተራድዖ ሚንስቴር ለዶይቸ ቨለ በጣም ጠቀሚው ተጓዳኝ ነው። በኅብረትም ፤ የጋዜጠኝነት ትምህርትና ጥራት፣ የመገናኛ ብዙኀንም ችሎታ በአዳጊ አገሮች፤ ከዚያም ላቅ ያለ ዕድገት በማስመዝገብ ላይ የሚገኙ አገሮች እንዲጠናከር ይረዳሉ። በያመቱ፤ 3,000 ገደማ ለሚሆኑ ሰዎች የመገናኛ ብዙኀን መደበኛና ማጠናከሪያ ትምህርት ይሰጣል። በማስተርስ ዲግሪ የ«ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኀን ትምህርት» የሚሰጠው ዶይቸ ቨለ ፤ ይኸው ተቋሙ ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ ከጀርመንም መሪ መሆኑ ነው የሚነገርለት።
እ ጎ አ በ 1953 ተግባሩን የጀመረው ዓለም አቀፍ የራዲዮና የመገናኛ ብዙኀን ድርጅት በሚያስደንቅ ሁኔታ ለውጦች አሳይቷል። ተግዳሮቶችን ለመቋቋም በቀጣይነት እንዳመቺነቱ ጥረት የማያድርግ አሠራጭ ድርጅት በፍጥነት ነው የሚከስመው ።
የዲጂታል ዝግጅቶችን በማሰናዳት ማሠራጨት የጀመርነው እጅግ ቀደም ብለን ነው፤ በጀርመን ከሚገኙ የመገናኛ ብዙኀን ድርጅቶች፣ ቀደም ብሎ በኢንተርኔት መጠቀም የጀመረ፣ በተለያዩ የህዝብ መገናኛ ዘዴዎችም በማትኮር ግንባር ቀደሙ ዶቸ ቨለ ነው ሲሉም ፤ ኤሪክ በተርማን አስረድተዋል።

ዮሐንስ ሆፍማን
ተክሌ የኋላ
አርያም ተክሌ