በማዳመጥ መማር የተሰኘው በዶቼቬለ እና በጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትብብር የሚቀርበው አዝናኝ እና ትምህርታዊ ተከታታይ ድራማ 6ኛ ዙር ቀረፃ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
የተመሰረተበትን የወርቅ እዮቢልዩ ማለት 50ኛ ዓመት መታሰብያ ነገ ለማክበር ዝግጅት ላይ ያለዉ በኔዘርላንድ የሚገኘዉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዉ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል በክብር እንግድነት የጋበዘዉ ጋዜጠኛ እና የሰብዓዊና ዴሞክራሲ መብት ተከራካሪዉ እስክንድር ነጋ ከጉዞ መታገዱ እንዳሳዘነዉ ገለፀ።
ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ በትናንትናዉ ዕለት ያዋቀሩት አዲስ ካቢኔ የለዉጥ ሽታ የሌለዉና የህዝቡን ጥያቄ የሚመልስ አይደለም ሲሉ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮች አስታወቁ።ተሿሚወቹ ህዝብን በቅንነት ማገልገል የሚችሉና ከተመደቡበት ቦታ ጋር ተያያዥነት ያለዉ የሙያ ባለቤቶች ሊሆኑ ይገባ ነበርም ብለዋል።