የደቡብ ሱዳን ጦርነትና መፍትሔዉ | አፍሪቃ | DW | 15.07.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የደቡብ ሱዳን ጦርነትና መፍትሔዉ

ደቡብ ሱዳን ከሠሜን ሱዳን ተገንጥላ ነፃ መንግሥት ከመሠረተች ባለፈዉ ሳምንት አራተኛ ዓመትዋን ብትደፍንም «ከጦርነት ወጣሕ» ተብሎ ከጦርነት ለሚማገደዉ ለሐገሪቱ ሕዝብ ነፃነቱ የፈየደዉ ነገር የለም።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:56

የደቡብ ሱዳን ጦርነትና መፍትሔዉ

ዓመት ከመንፈቅ ያስቆጠረዉን የደቡብ ሱዳንን የርስ በርስ ጦርነት በሠላም ለምፍታት የአካባቢዉ መንግሥታትም፤ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብም ያደረጉት ጥረት ለዉጤት አልበቃም።ደቡብ ሱዳን ከሠሜን ሱዳን ተገንጥላ ነፃ መንግሥት ከመሠረተች ባለፈዉ ሳምንት አራተኛ ዓመትዋን ብትደፍንም «ከጦርነት ወጣሕ» ተብሎ ከጦርነት ለሚማገደዉ ለሐገሪቱ ሕዝብ ነፃነቱ የፈየደዉ ነገር የለም።ኢትዮጵያዊዉ ምሑር ዶክተር ደረጃ ፈይሳ እንደሚሉት የጦርነቱ ምክንያት በተደጋጋሚ እንደሚነገረዉ የደቡብ ሱዳን ፖለቲከኞች ጠብ ብቻ አይደለም፤ጦርነቱን ለማስቆም የተደረገዉ ጥረት የከሸፈዉም አደራዳሪዎች በሽምግልናና የየራስ ጥቅምን በማስጠበቅ መሐል ሥለሚዋዥቁ ነዉ።ዶክተር ደረጀ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተባባሪ ፕሮፌሰርና ኦስሎ-ኖርዌ የሚገኘዉ ዓለም አቀፍ የሕግና የመርሕ ተቋም (ILPI) የአፍሪቃ ምርምር ሐላፊ ናቸዉ። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ አነጋግሯቸዋል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic