የዩጋንዳ ምርጫ | አፍሪቃ | DW | 11.02.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የዩጋንዳ ምርጫ

በመጪዉ ሳምንት በሚደረገዉ ምርጫ የተፎካካሪዎች አብይ ርዕሥ የሆነዉ ግን የሥራ አጥነት ፤ የመሠረተ-ልማት አዉታር እና ሙስና ናቸዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:12

የዩጋንዳ ምርጫ

የቀድሞዉ የዩጋንዳ አምባገነን መሪ ኢዲ አሚን ዳዳ በሐገሪቱ ለሚደረገዉ ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳ ማድመቂያ ሆነዋል።ለፕሬዝደንትነት ከሚወዳደሩት ፖለቲከኞች አንዱ አማም ምባባዚ ከተመረጡ በስደት የሞቱትን የኢዲ አሚንን አስከሬን ወደ ዩጋንዳ ለማስመጣት እና ቤተ-መዘክር ለመሰየም ቃል ገብተዋል።በመጪዉ ሳምንት በሚደረገዉ ምርጫ የተፎካካሪዎች አብይ ርዕሥ የሆነዉ ግን የሥራ አጥነት ፤ የመሠረተ-ልማት አዉታር እና ሙስና ናቸዉ።የናይሮቢዉ ወኪላችን ፋሲል ግርማ እንደተከታተለዉ በምርጫዉ ሐገሪቱን ለሠላሳ ዓመት የገዙት ዩሬ ሙሴቬኒ መሸነፋቸዉ አጠራጣሪ ነዉ።ፋሲል በሥልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ፋሲል ግርማ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic