የዚግፍሪድ ፓውዘባንግ ዜና ዕረፍት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 19.04.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የዚግፍሪድ ፓውዘባንግ ዜና ዕረፍት

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት እንዲከበር እና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲመሠረት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉት ጀርመናዊ የማህበራዊ ሳይንስ ምሁር ፕሮፌሰር ዚግፍሪድ ፓውዘንቫንግ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው፣ ኢትዮጵያውያን ወዳጆቻቸውና ባልደረቦቻቸው ኀዘናቸውን

Äthiopien: Landschaft In einer fruchtbaren, grünen Ebene in Äthiopien stehen kleine Hütten. Undatierte Aufnahme.

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት እንዲከበር እና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲመሠረት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉት ጀርመናዊ የማህበራዊ ሳይንስ ምሁር ፕሮፌሰር ዚግፍሪድ ፓውዘንቫንግ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው፣ ኢትዮጵያውያን ወዳጆቻቸውና ባልደረቦቻቸው ኀዘናቸውን እየገለጡ ነው።

ፕሮፌሰር ዚግፍሪድ ፓውዘንቫንግ ከ40 አመታት በላይ በኢትዮጵያ በተለይም በሰብዓዊ መብት እና ዲሞክራሲ በማስፈኑ ሂደት ላይ በማስተማር እና ስልጠና በመስጠት ይታወቃሉ። የጀርመናዊው የማህበራዊ ሳይንስ ምሁር የዕረፍት ዜና ቤተሰቦቻቸውን፣ ባልደረባዎቻቸውን እና የሚያደንቋቸው ኢትዮጵያንን አሳዝኗል። የፓውዘንቫንግ የረጅም ጊዜ ባልደረባ፤ ፕሮፌሰር ኪዬቲል ትሮንቮል ምሁሩን እንደሚከተለው ይገልጿቸዋል።

« ዚግፍሪድ ፓውዘንቫንግ እጅግ ጥሩ ሰው እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነበሩ። በተለይ በአፍሪቃ እና በኢትዮጵያ ላይ ያላቸውን አጠቃላይ የማህበራዊ ሳይንስ እውቀት በተለይ፣ በእድገት፣ በሰብዓዊ መብት እና ዲሞክራሲያዊ ሂደት ላይ ያደረጉትን ንድፈ ሀሳቦች በመጠቀም በአንድ አገር እና አካባቢዋ ላይ በተግባር አውለዋል። »

Autor: Ludger Schadomsky Copyright: Ludger Schadomsky/DW Titel: Wahl in Oromia, Äthiopien 23.Mai 2010 Thema: bei Äthiopiens Parlamentswahl 2010 wird diesem Wähler in Nazareth, Oromia, nach Aushändigung des Wahlzettels der Daumen mit Tinte bemalt, um einer Mehrfachabstimmung und damit Wahlbetrug vorzubeugen. Schlagwörter:Wahl Äthiopien 2010, Stimmabgabe, Polls, Voting Ethiopia 2010

በኦሮሚያ ክልል ምርጫ ሲካሄድ

ፕሮፌሰር ዚግፍሪድ ፓውዘንቫንግ ውስብስብ የሆኑ ጉዳዩችን ከስራቸው ጀምረው በመመልከት ፤ የእያንዳንዱን ተናጥል ኢትዮጵያዊ ፍላጎት ለመመልከት ችለዋል ይላሉ የረጅም ጊዜ ባልደረባቸው። ዚግፍሪድ ፓውዘንቫንግ ሶስት ጊዜ የኢትዮጵያ የምርጫ ታዛቢ ነበሩ። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይም በርካታ መፃፅህፍቶች አሳትመዋል።

«ሲግፍሪድ በሰፊው በኢትዮጵያ እድገት ላይ ያተኮሩ በርካታ መፃህፍት እና ትምህርታዊ የሆኑ ዘገባዎች አሳትመዋል። እንዲሁም በኢትዮጵያ ስላለው የዲሞክሪያሳዊ ሂደት ላይ- በተለይ ዲሞክራሲን ከበታች ሕብረተሰብ ስላለው አቀባበል ፅፈዋል። ይህንን ደረጃዊ ክስተቶች መዝግበውም እንደ አማካሪ እና ዘጋቢ በኢትዮጵያ የዲሞክሪያሳዊ ሂደት ላይ አስተዋፅዎ አድርገዋል። በተቃዋሚ ኃይላት መካከል መስማማት እንዲፈጠር፣ ሰላም ሊሰፍን የሚችልበትን አጀንዳዎች በማንሳት እና እያንዳንዱ ሰው በኢትዮጵያ ሰላም፣ መረጋጋት እና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን አንድ ዓይነት እና ሚዛናዊ ዕይታ እንዲኖረው ጥረዋል።»

ፕሮፌሰር ትሮንቮል እንደገለፁልት ፕሮፌሰር ዚግፍሪድ ፓውዘንቫንግ ያደረባቸውን የካንሰር ህመም ለመታከም ሆስፒታል በነበሩት የመጨረሻ ሳምንታት እንኳ በኖርዌይ የኢትዮጵያ ተገን ጠያቂዎች ላይ ይሰሩ ነበር። ለምን የዚህን ያህል በኢትዮጵያ ላይ አተኮሩ? አላማቸው ምን ነበር?

Autor: Ludger Schadomsky Copyright: Ludger Schadomsky/DW Titel: Hauptcampus der Universität Addis Abeba (AAU) Thema: Die Universität Addis Abeba (AAU) ist traditionell ein Hort der politischen Opposition. Die Proteste gegen die Wahlfälschungen 2005 wurden nicht zuletzt von Studenten auf die Straße getragen. Sicherheitskräfte patroullieren derzeit verstärkt auf dem Campus Schlagwörter: Universität Addis Abeba, University of Addis Ababa (AAU), Proteste 2005, Wahl Äthiopien 2010, Ethiopia 2010

የአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ ዮንቨርሲቲ

« የማህበራዊ ሳይንስ ልማት ላይ የፕሮፌሰርነት ትምህርታቸውን እንደአጠናቀቁ በዛን ሰአት በሀይለ ሥላሴ ዮንቨርሲቲ እረዳት ፕሮፌሰር ሆነው ስራ አገኙ። እኢአ 1967 ወደ ኢትዮጵያ ሄደው እዛ መኖር እና መስራት ጀመሩ፤ የንጉሱ አመራር 1974 ዓ ም እስኪወድቅ ድረስ! በየከተማው እየተዘዋወሩ፣ የማህበረሰቡን አኗኗር ያጠኑ ነበር። እና ከመጀመሪያው የስራ ዕድላቸው ጀምረው በኢትዮጵያ ተስበው ነበር ። ይህንንም አላማቸውን በመቀጠል 45 አመት የሙያ ህይወታቸውን አሳልፈዋል።»

እኚህ ታዋቂ ሰው ዛሬ በህይወት የሉም። ይሁንና ካደረጉት አስተዋፅዎ አንፃር በተለያየ አቅጣጫ ልናስታውሳቸው የምንችልበት ምክንያቶች አሉ ይላሉ ፕሮፌሰር ትሮንቮል« መፃህፎቻቸው እና ዘገባዎቻቸው የአሁኑን እና የወደፊቱን የኢትዮጵያ ስራዎች ማመሳከሪያ ይሆናሉ። እንደ ታታሪ ሰው፣ እንደ አለም አቀፍ ዜጋ፣ ይታወሳሉ። በኢትዮጵያ ዲሞክራሲዊ እና ፖለቲካዊ ነፃነት የመፍቀድ ሂደት ላይ እንደ አንድ ግለሰብ ደግሞ አስተዋፅዎ ያደረጉም ጭምር። »

ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic