የሚኒስቴር መሥራያ ቤቱ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ግንባታው ከ60 ከመቶ በላይ ተከናውኗል ካሉት ግድብ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከግብጽም ከሱዳንም ጋር በትብብር መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የምትሰራውን የታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ማንም ሊያስቆም እንደማይችል አስታወቀች።የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ግንባታው ከ60 ከመቶ በላይ ተከናውኗል ካሉት ግድብ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከግብጽም ከሱዳንም ጋር በትብብር መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። በቅርቡ በሚኒስትሮች ደረጃ ካይሮ ውስጥ በተካሄደው የሦስትዮሽ ስብሰባ ላይ ፣ በግብጽ መገናኛ ብዙሀን እንደተዘገበው ኢትዮጵያ የማሻሻያ ሀሳብ ሳይሆን የማብራሪያ ጥያቄዎችን ማቅረቧን ተናግረዋል። መሰል መረጃዎችን እንዳሉ የሚያቀርቡ የኢትዮጵያ መገኛኛ ብዙሀንንም ተችተዋል። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ተጨማሪ ዘገባ አለው።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ