የእጩ ራይላ ኦዲንጋ ራሳቸውን ከፕሬዚደንታዊው ምርጫ ማግለል | አፍሪቃ | DW | 10.10.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የእጩ ራይላ ኦዲንጋ ራሳቸውን ከፕሬዚደንታዊው ምርጫ ማግለል

የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ህብረት፣ በምህጻሩ የናሳ እጩ ራይላ ኦዲንጋ በጎርጎሪዮሳዊው የፊታችን ጥቅምት 26፣ 2017 በሚደረገዉ ድጋሚ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እንደማይወዳደሩ ዛሬ አስታወቁ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:48
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
02:48 ደቂቃ

«ዉሳኔያቸዉ የሀገሪቱን ፖለቲካ ቀዉስ ያባብሳል፤»

ኦዲንጋ በሀገሪቱ አስመራጭ ኮሚሽን ላይ  እና በምርጫ ሕጉ ላይ ለውጦች እና ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ከመጀመሪያው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ሂደት ወዲህ ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች የሚጠብቁትን መልስ ካላገኙ በድጋሚው ምርጫ እንደማይሳተፉ ያሰሙትን ዛቻ አሁን በዚሁ ውሳኔአቸው እውን አድርገውታል። ይህን ዉሳኔያቸዉንም በደብዳቤ ለሚመለከተዉ መንግሥታዊ አካል አቅርበዋል። ይኸው የራይላ ኦዲንጋ ውሳኔ ለመጻዒው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ምን ተፅዕኖ ይኖረዋል?  ሸዋዬ ለገሠ ናይሮቢ የሚገኙትን አቶ ፍቅረማርያም መኮንንን በስልክ አነጋግራቸዋለች።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic