የኤርትራ ነፃነትና የሕዝቧ ፍዳ | አፍሪቃ | DW | 10.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የኤርትራ ነፃነትና የሕዝቧ ፍዳ

ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል ኤርትራን ከዓለም ከፍተኛ ጭቆና የሚፈፀምባት፥ ዝግና ድብቅ ሐገር ይላታል።አንዲት ኤርትራዊት የመብት ተማጓች በበኩላቸዉ በዜጎቹ ላይ ግፍ በመፈፀም የኤርትራን መንግሥት የሚወዳደር ሥርዓት ካለ ምናልባት የሰሜን ኮሪያዉ ነዉ።

ኤርትራ የራስዋን ነፃ መንግሥት በይፋ ከመሠረተች ከሁለት ሳምንት በሕዋላ ሃያ-ዓመት ትደፍናለች። ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶችና በስደት የሚኖሩ ኤርትራዉያን እንደሚሉት ግን ሃያ-ዓመቱ ለአብዛኛዉ ኤርትራዊ የነፃነት ሳይሆን የጭቆና፥የእስራት፥ የስደትና እንግልት ዘመን ነዉ።ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል ኤርትራን ከዓለም ከፍተኛ ጭቆና የሚፈፀምባት፥ ዝግና ድብቅ ሐገር ይላታል።አንዲት ኤርትራዊት የመብት ተማጓች በበኩላቸዉ በዜጎቹ ላይ ግፍ በመፈፀም የኤርትራን መንግሥት የሚወዳደር ሥርዓት ካለ ምናልባት የሰሜን ኮሪያዉ ነዉ።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።

ድልነሳ ጌታነሕ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic