የኢድ አል ፈጥር በዓል | ኢትዮጵያ | DW | 17.07.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢድ አል ፈጥር በዓል

የሙስሊሙ ማህበረሰብ ያለፈውን አንድ ወር በፆም ፣ በፀሎት እንዲሁም በመረዳዳት አሳልፎ ዛሬ 1436ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓልን አከበረ። በዓሉ ከፍተኛ ጥበቃ በነበረት በአዲስ አበባ ስታድየም የተከበረ ሲሆን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ሼህ መሀመድ ኑር ስለበዓሉ ምንነት ለዶቼ ቬለ አስረድተዋል።

በበርካታ ሃገራት ዛሬ የአንድ ወሩ የሙስሊሞች የፆም ወራት ማለትም ሮመዳን ያበቃበት በዓል ተከብሮ ዋለ። አንድ ሺህ አራት መቶ ሰላሳ ስድስተኛዉ የኢድአልፈጥር በዓል ኢትዮጵያ ዉስጥም በተለይ አዲስ አበባ ላይ በደማቅ ሥርዓት መከበሩን ዘጋቢያችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ በላከልን ዘገባ አመልክቷል።ሮመዳን ያበቃበት ዕለት ዛሬ ሲታሰብ ግን የእምነቱ ተከታዮች በሚበዙባቸዉ በተለያዩ ሃገራት አጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃት መድረሱን ዘገባዎች ያመለክታሉ። የሶማሊያዉ ፅንፈኛ እስላማዊ ቡድን የአሸባብ መሪ ዕለቱን አስመልክተዉ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት አዳዲስ ተመልማዮች ቡድናቸዉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አስተላልፈዋል። በቡድኑ ድረገጽ ላይ የወጣዉ አህመድ ኦማር አቡ ሁባይዳ በመባል የሚታወቁት አህመድ ዲሪየ መግለጫ አክሎም የሙጃሂዲን ጦር እንደተሳለ እና በሀገሪቱ ያሉትን ጠላቶች እንደሚያጠቃ በመግለጽ፤ ኢአማንያን ያሏቸዉ ላይ ጥቃቱ እንዲጠናከር ጥሪ አቅርቧል። በምሥራቅ አፍሪቃ የሚገኙ ሙስሊሞች ስቃይ እንዲያበቃም ፈጣሪን የተማፀነዉ የአሸባብ መሪ መልዕክት በኬንያ ቅኝ ግዛት ሥር ናቸዉ ላላቸዉ ሙስሊሞች ወንድሞቻቸዉ እነሱን ለመርዳት እንደማይቦዝኑ ገልጿል።

እንደ ጋና እና ኬንያ ያሉት ሀገራት በዓሉን ነገ ቢያከብሩም፤ በአብዛኞቹ የዓለማችን ክፍሎች ፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ኢድ አል ፈጥር ዛሬ ተከብሯል።የበዓሉን አከባበርም አስመልክቶ በአዲስ አበባ ስታዲዮም የተደረገውን ስነ ስርዓት በስፍራው የሚገኘው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታትሏል።

አብዛኛው የሙስሊሙ ማህበረሰብ፤ እቤቱ ተከብስቦ ከቤተሰቡ ጋር ዘና እያለ ቢያሳልፍም፤ በዛሬው ቀን ስራ መስራት ያለባቸው ሙስሊሞችም አልጠፉም። አሁንም ከአዲስ አበባ ሳንወጣ ሌላው የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ዮሀንስ ገብረ እግዚያብሄር እየተዘዋወረ የስራ ሁኔታቸው አስገድዷቸው ፆሙን እና በዓሉን ስራ ቦታ ያሳለፉ ኢትዮጵያውያንን አነጋግሯል።

እንዲሁም በሳውዲ አረቢያ እና ጀርመን የሚገኙ ጥቂት ሙስሊማውያንም ፤ የኢድ አል ፈጥርን በዓል ፤ ምንም እንኳን ከሀገር ውጪም ቢሆን እያከበርን ነው ብለውናል። በዓሉን እንዴት እያሳለፉ እንደሆነ እናስደምጣችሁ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ዮሀንስ ገብረ እግዚያብሄር

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic