የኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ወደ መኢአድ መሪነት መመለስ | ኢትዮጵያ | DW | 27.12.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ወደ መኢአድ መሪነት መመለስ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ቅዳሜ እና ዕሁድ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ከፖለቲካው ዓለም ራሳቸውን እንዳገለሉ የተናገሩትን የድርጅቱን ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ኃይሉ ሻውልን በድጋሚ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ድርጅቱን እንዲመሩ መርጧል ።

default

ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ይህን የፓርቲውን ከፍተኛ ሥልጣን ለሌላ ያስረክባሉ ተብሎ ሲጠበቅ ነበር ። ጠቅላላ ጉባኤው ከዚህ ሌላ ከአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ጋር መኢአድ ለመዋሀድ የጀመረው ድርድር ተግባራዊ እንዲሆንም በሙሉ ድምፅ ወመሰኑን የአዲስ አበባው ወኪላችን ታደሰ ዕንግዳው ዘግቧል ። ታደሰ ዕንግዳው ፣ ሂሩት መለሰ ነጋሽ መሀመድ