የኢትዮ-አሜሪካዉያን ተቃዉሞ ሠልፍ | ኢትዮጵያ | DW | 03.08.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮ-አሜሪካዉያን ተቃዉሞ ሠልፍ

የኢትዮጵያ መንግሥት ያሠራቸዉን ሙስሊሞችንና የሙስሊም መሪዎችን እንዲፈታ ጠይቀዋል።ዩናይትድ ስቴትስም፥ ሠልፈኞቹ «የሕዝብ መብት ይረግጣል» ላሉት ለኢትዮጵያ መንግሥት የምትሠጠዉን ርዳታና ድጋፍ ዳግም እንዲታጤነዉ በደብዳቤ አቤት ብለዋል።

***Für mögliche Ergänzungen der Karte, wie z.B. andere Sprachen, zusätzliche Orte oder Markierungskreuz, wenden Sie sich bitte an infografik@dw-world.de (-2566), Außerhalb der Bürozeiten an bilder@dw-world.de (-2555).*** DW-Grafik: Per Sander 2011_03_10_Laender_Prio_A_B

የኢትዮ-አሜሪካዉያን ተቃዉሞ ሠልፍ

የኢትዮጵያ መንግሥት ሐማኖታዊ ነፃነታቸዉና መብታቸዉ እንዲከበር በጠየቁ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ላይ የሚወስደዉን የሐይል እርምጃ እንዲያቆም በሁለት የዩናይትድ ስቴትስ ትላልቅ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን-አሜሪካዉያን ሙስሊሞችና የመብት ተሟጋቾች በሠልፍ ጠየቁ።ዋሽንግተን ዲሲና ሲያትል ከተሞች ትናንት አደባባይ የወጡት ሠልፈኞች የኢትዮጵያ መንግሥት ያሠራቸዉን ሙስሊሞችንና የሙስሊም መሪዎችን እንዲፈታ ጠይቀዋል።ዩናይትድ ስቴትስም፥ ሠልፈኞቹ «የሕዝብ መብት ይረግጣል» ላሉት ለኢትዮጵያ መንግሥት የምትሠጠዉን ርዳታና ድጋፍ ዳግም እንዲታጤነዉ በደብዳቤ አቤት ብለዋል።የዋሽንግተን ዲሲዉ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic