የኢትዮጽያ ፈላሻሞራዎች ላይ የደረሰ ችግር | ኢትዮጵያ | DW | 21.01.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጽያ ፈላሻሞራዎች ላይ የደረሰ ችግር

የእስራኤል ልጆች እበትናችኋለሁ እንዲሁም እሰበስባችኋለሁ የሚለዉን የተስፋ ቃል ይዘዉ ባለፉት 20 አመታት ወደ እስራኤል ለመሄድ ሃብት ንብረታቸዉን በትነዉ ጓዛቸዉን ጠቅልለዉ ወደ እስራኤል ለመጓዝ ያሰቡ

default

ከ 20 ሺ በላይ የኢትዮጽያ ፈላሻሞራዎች መሄድ ስላልቻልን ከሁለት ያጣን ሆነናል ሲሉ መግለጻቸዉን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ዘግቦአል። በእስራኤል የሚገኙት እትዮጽያዉያን ደግሞ ሴቶች ማህጸናቸዉ ጽንስ እንዳይዝ የሚያደርግ ክትባት ለረጅም አመታት እየተሰጣቸዉ መሆኑና በስራም ሆነ በሌሎች ቦታዎች የዘርኝነት መድሎ የለት ተለት ገጠመኛቸዉ መሆኑ እየገለጹ ነዉ። ድርጊቱ በሚስጥር የተያዘበት እና የተጎዱ ሰዎች መብታችንን እናጣለን በሚል ይፋ መናገር ባልቻሉበት የድምጽ እና የስእል ዋቢ ማግኘት ባይቻልም ወኪላችን ዜናነህ መኮንን በእስራኤል ሂብሪ ዩንቨርስቲ ምሁርየሆኑትን አነጋግሮ ዘገባ አድርሶልናል

ዜናነህ መኮንን ፣ ታደሰ እንግዳዉ

አዜብ ታደሰ፣ ሂሩት መለሰ