1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የጋዜጦች አምድ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር በበርሊን

11.11.2004 የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በሁለት ቀኑ ይፋ የጀርመን ጉብኝታቸው በበርሊን ከመራሔ መንግሥት ጌርሀርት ሽረደር ከፕሬዚደንት ሆርስት ከለር፡ ከውጭ ጉዳይ ዮሽካ ፊሸር እና ከኤኮኖሚ ተራድዖ ሚንስትር ወይዘሮ ሀይደማሪ ቪችሶሬክ ሶያል ጋር ተገናኝተው ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

ከመራሔ መንግሥቱ ጋር ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከል በተለይ የሁለቱ ሀገሮች የልማት ትብብር ልዩውን ትኩረት አግኝቶዋል።
ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር የጀመረችውን የልማት ትብብር በበለጠ ደረጃ ለማሳደግ እንደምትፈልግ ሽረደር ከጠቅላይ ሚንስትር መለስ ጋር በሰጡት የጋራ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል። ጀርመን በተለይ ለኢትዮጵያ በግንባታው ዘርፍ ልታደርገውን የምትችለውን በተመለከተ ሽረደር ሲያብራሩ፡ «በተለይ በግንባታው ዘርፍ የኢትዮጵያውያን ሙያተኝን ሥልጠና ልናፋጥን የምንችልበትንና ጀርመንም በዚሁ ረገድ ልታበርክተው የምትችለውን አስተዋፅኦኣ በጋራ ለማፈላለግ ወስነናል። ምክንያቱም ኢትዮጵያ በሥልጠናው ዘርፍ ከጀርመን ተሞክሮ ትምህርት ለመውሰድ ትልቅ ፍላጎት አሳይታለችና።»
ሽረደር ባለፈው ጥር ወር ኢትዮጵያን በጎበኙበት ጊዜ በሀገኦቻቸው የተሐድሶ ለውጥ ለማነቃቃት ዝግጁ ለሆኑ ኢትዮጵያን ለመሳሰሉ አፍሪቃውያት ሀገሮች ዪሰጠውን የልማት ርዳታ ማጠናከሩ የተሳካ ውጤት ከማስገኘቱም ሌላ፡ አህጉሩን አስተማማኝ እንደሚያደርግና ሰላምም እንደሚያወርድ መግለቸው የሚታወስ ነው።
ያካባቢ በተለይም የአፍሪቃን ቀንድ የሚመለከቱ ጉዳዮችም ሁለቱ ባለሥልጣናት የተወያዩባቸው ሌሎች አርዕስት ነበሩ። በተለይ ኢትዮጵያ ለሱዳን ውዝግብ መፍትሔ በማፈላለጉ ጥረት ላይ የያዘችውን ሚና መራሔ መንግውቱ ሳያሞግሱ ኣለፉም። ቀደም ሲልም፡ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ በዶቸ ቬለ አዘጋጅነት ከጀርመናውያን ጋዜጠኞች ጋር ባካሄዱት ሰፋ ያለ ውይይት ለሰሜን ደቡብ ውዝግብ ሰላማዊ መፍትሔ የሚገኝበት ድርጊት ለዳርፉር ውዝግብ ለሚያበቃበት ሁኔታ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በመቀጠለም ፌዴራዊው ሥርኳትና ሰፊ ራስ ገዝ አስተዳደር በሱዳን ውዝግብ ድርድር ላይ ትልቅ ሚና መጫወቱን በማስታወቅ፡ ፌዴራሊዝም ለዳርፉርም መፍትሔ ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል።
በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለተፈጠረውና እስካሁን እልባት ያልተገኘለትን የድንበር ውዝግብ በተመለከተም ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰጡት አስተያየታቸው፡ « ሁለቱ ወገኖች አግባቢ አስማሚ መፍትሔ ማግኘት ይቻል ዘንድ ለመነጋገር ፈቃደኞች ከሆኑ ለድንበር ውዝግቡና ለችግሩ መን?ሥዓ መፍትሔ ሊገኝ ይችላል። ኢትዮጵያ ልዩነታችንን በኃይሉ ተግባር ለመፍታት እንደማትፈልግ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ አስታውቃለች። ኤርትራውያኑ ወንድሞቻችንም በዚህ ላይ አዎንታዊ መልስ እንደሚሰጡ ተስፋ እናደርጋለን፡ እንጠብቃለንም፡ በእኛ እና በኤርትራ መካከል ልዩነታችንን በጠቅላላ በተጨባጭ መንገድ ለመፍታትም ውይይት እንዲደረግ ጠይቀናል። በኤርትራ ያሉ ወንድሞቻችንም ቀና መልስ እንደሚሰጡ ተስፋ እናደርጋለን። »
ከዚህ ሌላም ኢትዮጵያን ረሀብንና ድህነት ለመታገል በምታደርገው ትረት ላይ የዓለም አቀፍፉ ኅብረተ ሰብ ርዳታ ተጓድሎ ነበር በሚል ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ከጥቂት ጊዜ በፊት ቅሬታቸውን ቢገልጹም በዚኦኢሁ ሁኔታ ዙርያ ለውጥ መኖሩን ሲጠቅሱ፡ እንዲህ ነበር ያሉት « የልማቱን ርዳታ በተመለከተ የተቀየረ ነገር አለ። በወቅቱ የምግብ ርዳታ በማከፋፈል ላይ ብቻ ሳይሆን የረሀቡን መንሥዔም በመታገሉ ድርጊት ላይ አትኩረናል፤ ትኩረታችንንም ኢትዮጵያውያንን በምግቡ አቅርቦት ራስ አገዝ በማድረጉ ሂደት ላይ አሳርፈናል። »