የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግሮች ና አንድምታው | ኢትዮጵያ | DW | 18.08.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግሮች ና አንድምታው

በኢትዮጵያ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አያያዝ አሁንም ማነጋገሩ ቀጥሏል ። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢትዮጵያ የሙስሊሞች የሐይማኖታዊ ነፃነት ጥያቄ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን በዚያው መጠን መንግሥት የሚወስደው እርምጃ እየጠነከረ ሄዷል ።

ዓለም ዓቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች የውጭ መንግሥታትና የሐገር ውስጥ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሃገሪቱ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንደማይከበሩ በየአጋጣሚው ማሳወቃቸው አልቆመም ። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ይህን አይቀበልም ። ከዚያ ይልቅ በህገ መንግሥቱ የሰፈሩትን እነዚህን መብቶች በማክበር ላይ መሆኑን ነው የሚገልፀው ። ሆኖም ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና የመብት ተሟጋቾች በፀረ ሽብርና በፕሬስ ህጉ ሰበብ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞችን መታሰራቸውን የመብት ጥያቄ ያነሱ ሙስሊሞችም ለሞት ለእስርና ለእንግልት መዳረጋቸው መቀጠሉን ይናገራሉ ። በቅርቡ የአደባባይ ሰልፍና ህዝባዊ ስብሰባዎች ያደራጁ ና ያካሄዱ የሐገር ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላቶቻቸው እስርና ወከባ እንደተፈፀመባቸው አስታውቀዋል ። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢትዮጵያ የሙስሊሞች የሐይማኖታዊ ነፃነት ጥያቄ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን በዚያው መጠን መንግሥት ጥያቄውን በሚያቀርቡ ወገኖች ላይ የሚወስደውም እርምጃ እየጠናከረና እየከፋ መጥቷል ። በተቃዋሚዎች ላይ ጠንክሯል ። ይህ እንዴት ይታያል ? ወዴትስ ያመራል ? በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲወያዩልን 3 እንግዶችን ጋብዘናል ። አቶ ግርማ ሰይፉ በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ፣ አምባሳደር ጥሩነህ ዜና የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ፣ እና አቶ ያሬድ በአሁኑ ሰዓት በስደት ላይ የሚገኙ የቀድሞ የሰብዓዊ መብት ጉባኤ አባል ናቸው ።

ሂሩት መለሰ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic