የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት | ኢትዮጵያ | DW | 11.09.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት

ኢትዮጵያዉያን ዛሬ የዘመን መለወጫ በዓልን በተለያየ ድግሥና ሥርዓት አክብረዉ ዉለዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ሁለት ሲዊድናዊ ጋዜጠኞችን ጨምሮ ከአንድ ሺሕ ዘጠኝ መቶ በላይ እስረኞችን በይቅርታ መልቀቁን አስታዉቋል።

ኢትዮጵያዉያን ዛሬ የዘመን መለወጫ በዓልን በተለያየ ድግሥና ሥርዓት አክብረዉ ዉለዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ሁለት ሲዊድናዊ ጋዜጠኞችን ጨምሮ ከአንድ ሺሕ ዘጠኝ መቶ በላይ እስረኞችን በይቅርታ መልቀቁን አስታዉቋል። በሁለት ሺሕ አራት በርካታ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፥ ነፃ ጋዜጠኞች፥የሐማኖት መብት ተሟጋቾች ታስረዋል፥ ተፈርዶባቸዋል፥ ወይም ተሰደዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት አብዛኞቹን ሰዎች ያሰረና ያስፈረደባቸዉ በአሸባሪነት እየወነጀለ ነዉ።ትናንት በይቅርታ መለቀቃቸዉ የተነገረዉ እስረኞች ከሁለቱ የሲዊድን ዜጎች በስተቀር የተቀሩት ማንነት እስካሁን በይፋ አልተገለጠም።አሮጌዉ ዓመት ከፖለቲካዉና ከሐይማኖታዊዉ ዉዝግብና ዉጣ ዉረድ በተጨማሪ ኢትዮጵያን ለሃያ-አንድ ዓመት ያሕል የመሩት ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊና ለሃያ-ዓመት ያሕል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትሪያርክ የነበሩት ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ-ጳዉሎስም ያረፉበት ዓመት ነበር።ከአዲስ አበባ የደረሱን ዘገቦች እንደሚጠቁሙት ሐዘኑና የኑሮ ዉድንነት የአዲስ አበባዉን የበዓል ፌስታ ተጫጭነዉታል።

ነጋሽ መሃመድ

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

 • ቀን 11.09.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink http://p.dw.com/p/166sb

ተዛማጅ ዘገባዎች

 • ቀን 11.09.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink http://p.dw.com/p/166sb