የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በሪዮ ኦሎምፒክ ዝቅተኛ ውጤት ካስመዘገበ በኋላ የኢትዮጵያ አትሌቲክ ፌዴሬሽን እና በአትሌት ኃይሌ ገብረ-ስላሴ የሚመራው የአትሌቶች ጊዜያዊ ኮሚቴ እሰጥ አገባ ላይ ናቸው።
አትሌት ኃይሌ ገብረ-ስላሴ፣ገዛኽኝ አበራ፣ ገ/እግዚአብሔር ገ/ማርያም፤ አሰለፈች መርጊያ፣ አሰልጣኝ ሻምበል ቶሎሳ ቆቱን ያካተተው ጊዜያዊ ኮሚቴ በሪዮ በተመዘገበው ዝቅተኛ ውጤት ምክንያት የኢትዮጵያ አትሌቲክ ፌዴሬሽን ስልጣኑን እንዲያስረክብ ጠይቋል። ፌዴሬሽኑ በበኩሉ አትሌቶቹ እና አመራሩ በመዋከቡ ውጤት ማምጣት አልተቻለም የሚል ምክንያት አቅርቧል። የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ አለባቸው ንጉሴ "የስልጣን ጊዜያችን ህዳር 24 ነው የሚጠናቀቀው።እስከ ህዳር 24 ሳንጠብቅ መስከረም ወይም ጥቅምት ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔ እንጠራለን።" ብለው ተናግረዋል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ