የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ወዴት? | ስፖርት | DW | 20.08.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ወዴት?

ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያ አትሌቶች በዓለም አቀፍ ዉድድሮች የሚያስመዘግቧቸዉ ድሎች እና የሚያገኟቸዉ ሜዳሊያዎች ቁጥር እየቀነሱ መምጣታቸዉ ይስተዋላል። ሰሞኑን ለንደን ላይ በተጠናቀቀዉ 16ኛዉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት የዉድድር መስክ ቢበረክትም የተገኘዉ 2 ወርቅ እና 3 የብር ባጠቃላይ 5 ሜዴሊያ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 29:58

የዘንድሮው ውጤት ከቀደሙት ውድድሮች አኳያ ቀንሷል

 ቀዳሚዎቹ ስመጥር አትሌቶች አስከብረዋቸዉ ከቆዩት ርቀቶች ዘንድሮ አልተገኙም። በተቃራኒዉ በ5000 ሜትር ለዓመታት ተወስዶ የነበረዉ ክብር ዘንድሮ ተመልሷል። ያም ሆኖ ግን ብዙዎች የጠበቁትን ያህል በዉጤቱ አልረኩም። አትሌቶቹም እንዲሁ። ብቸኛዉ የኢትዮጵያ መታወቂያ የሩጫ ስፖርት አሁን ድሉ የቅርብ ተፎካካሪ ወደሆነች ወደጎረቤት ኬንያ ፊቱን ያዞረ መስሏል ወይም አዙሯል። የኢትዮጵያ አትሌቲክ ፌዴሬሽን ዉስጠ ምስጢሩም በሚያዉቁት ባለድል አትሌቶች መመራት ከጀመረ አንድ ዓመት ቢሆነዉ ነዉ።  የአትሌቲክስ ስፖርቱ አሁን ወዴት እያመራ ነዉ? ዉጤት መራቁስ ለምን? ዶይቸ ቬለ ያደረገውን ውይይት ማድመጥ ይችላሉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic