የኢትዮጵያ መንግስት ከሳውዲ ዜጎቹን እንደሚያወጣ ኣስታወቀ | ራድዮ | DW | 11.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ራድዮ

የኢትዮጵያ መንግስት ከሳውዲ ዜጎቹን እንደሚያወጣ ኣስታወቀ

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ እንደገለጸው የኢትዮጵያ መንግስት ተመላሽ ስደተኞችን መዝግቦ ለመመለስ ከሳውዲ መንግስ ጋርም እየሰራ ይገኛል። ዓለም ዓቀፉ የሰራተኞች ተቐም ILM ም በዚህ ረገድ የኢትዮጵያን መንግስት ለመርዳት ከመንግስት ጋር ንግግር መጀመሩን ኣስታውቐል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ እንደገለጸው የኢትዮጵያ መንግስት ተመላሽ ስደተኞችን መዝግቦ ለመመለስ ከሳውዲ መንግስ ጋርም እየሰራ ይገኛል። ዓለም ዓቀፉ የሰራተኞች ተቐም ILM ም በዚህ ረገድ የኢትዮጵያን መንግስት ለመርዳት ከመንግስት ጋር ንግግር መጀመሩን ኣስታውቐል።

በሳውዲ የሚገኙ ኢትዮፕያውያን በዚያች ኣገር የሚገኘው የኢትዪጵያ ኢምባሲ ኣስፈላጊውን ትኩረት ኣልሰጠንም ሲሉ ያማርራሉ ጃፈር አሊ ዘውዳዊው የሳውዲ ኣረቢያ መንግስት በህገወጥ መንገድ ወደ ኣገሪቱ የገቡ ናቸው የሚላቸውን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የውጪ ዜጎችን ማስወጣት ወይንም ማደን ከጀመረ ቀናት ተቆጥረዋል። እስከትላንት ብቻ የሳውዲ ፖሊስ 17 000 ያህል የውጪ ዜጎችን ኣድኖ ማጎሩን ኣስታውቐል። ኣያያዙ ግን ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ሰብዓዊ እርህራሄ የጎደለው ከመሆኑም በላይ ፍጹም ጭካኔ የተመላበት መሆኑ ነው እየተነገረ ያለው።

በተለይም ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሚዘገንን መልኩ በሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች እየታደኑ እየተደበደቡና እየተዘረፉ መሆናቸው ተዘግቧል። በዚህም ሳያበቃ ለጊዜው ቁጥራቸው ባይረጋገጥም በጥይት ተደብድበው የሞቱም እንዳሉ ታውቐል። የተደፈሩ ኢትዮጵያት ሴቶችም እንዳሉ እየተሰማ ነው።

በተለይ የሟቾቹ ጉዳይ ኢትዮጵያውያንን እጅግ እያስቆጣ ባለበት በኣሁኑ ወቅት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ኣቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንደሚሉት የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹን ወደ ኣገራቸው ለመመለስ በዛሬው ዕለት ምዝገባ ጀምሯል።

Muslim pilgrims gather atop Mount Mercy on the plains of Arafat during the peak of the annual haj pilgrimage, near the holy city of Mecca October 14, 2013. An estimated two million Muslims were in Mecca, Saudi Arabia, on Monday morning for the start of the annual Haj pilgrimage. REUTERS/Ibraheem Abu Mustafa (SAUDI ARABIA - Tags: SOCIETY RELIGION)

Muslime Gebet auf dem Berg Arafat 14.10.2013

መመለሱ ኣንድ ነገር ሆኖ በርካቶች እንደሚሉት በዚያች ኣገር የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲም ሆነ በኣጠቃላይ የኢትዮጵያ መንግስት እየተፈጸመባቸው ካለው ኣሰቃቂ በደል ዜጎቹን ለመታደግ ከወዲሁ እያደረገ ያለው ጥረት በቂ ኣይደለም እየተባለነው። አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለዶቸቬሌ እንደገለጹት ግን መንግስታቸው ክስተቱን በቁጭት ነገር ግን በሰለጠነ መንገድ እየተከታተለው እና ኣስፈላጊውን ሁሉ በመፈጸም ላይ ይገኛል ብሏል።ምዝገባው እንደተጠናቀቀም በፍጥነት ወደ ኣገራቸው እንዲመጡ ይደረጋል ብሏል። የዓለም ዓቀፉ የሰራተኞች ተቐም ILO ተወካይ ወ/ሮ ኣይዳ አወል እንደሚሉት ደግሞ ድርጅታቸው በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት እየመከረ ሲሆን በተለይም ሳውዲ አረቢያ ላይ ከተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቐማት ጋር ለተመላሽ ስደተኞች በተለይም ለሶቶች እና ህጻናት የኣስቸኩዋይ ጊዜ እርዳታ ስለሚደርስበት ሁኔታ እየተነጋገሩ መሆናቸውን ገልጿል።

ከሞላጎደል ሴቶች የሆኑ በርካታ ኢትዮጵያውያን በየዓመቱ ስራ ፍለጋ ወደ ማዕከላዊው ምስራቅ እንደሚሰደዱ ይታወቃል። በILO መረጃዎች መሰረት ባለፈው ዓመት ብቻ 200 000 ያህል ኢትዮጵያውያን ወደዚያው ተሰዷል። 91 ሚሊየን ከሚገመተው የኢትዮጵያ ህዝብ ILO እንደሚለውk ከ20 በመቶ በላይ የሚሆኑት ስራ ኣጥ ናቸው።

ጃፈር ዓሊ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic