የኢትዮጵያ መንግሥትና የበርሊኑ ጉባኤ | ኢትዮጵያ | DW | 22.02.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ መንግሥትና የበርሊኑ ጉባኤ

የኢትዮጵያ ጉዳይ አጥኚ ፕሮፌሰር ሽቴፋን ብሩነ ትናንት በርሊን ዉስጥ በተደረገ ሥብሰባ ላይ እንዳሉትየኢትዮጵያን የወደፊት ሒደት ማወቅ የሚቻለዉ በገዢዉ ፓርቲ መሪዎች መሐል ያለዉ የሐይል አሰላለፍ በግልፅ ሲታወቅ ነዉ።«

ከቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ከአቶ መለስ ዜናዊ ሕለፈት በሕዋላ የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ሒደት በትክክል ማወቅ እንደማይቻል አንድ ጀርመናዊ ምሑር አስታወቁ።በሐምቡርግ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ጉዳይ አጥኚ ፕሮፌሰር ሽቴፋን ብሩነ ትናንት በርሊን ዉስጥ በተደረገ ሥብሰባ ላይ እንዳሉትየኢትዮጵያን የወደፊት ሒደት ማወቅ የሚቻለዉ በገዢዉ ፓርቲ መሪዎች መሐል ያለዉ የሐይል አሰላለፍ በግልፅ ሲታወቅ ነዉ።«ኢትዮጵያ ከመለስ በሕዋላ» በሚል ርዕሥ ትናንት በርሊን ዉስጥ በተደረገዉ ዉይይት ላይ የተገኙት በጀርመን የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳይ ምክትል ሐላፊ ሆልገር ክሬመርን በበኩላቸዉ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር መደራደር «ከባድ» እንደሆነ አስታዉቀዋል።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል እንደዘገበዉ በዉይይቱ በርካታ ሰዎች ተካፍለዋል።አያሌ የኢትዮጵያ ጉዳዮችም ተዳሰዋል።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች