የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት አያያዝ የሚተቸው የውሳኔ ሐሳብ እያወዛገበ ነው | ዓለም | DW | 02.11.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት አያያዝ የሚተቸው የውሳኔ ሐሳብ እያወዛገበ ነው

አሜሪካዊው የሕግ-መወሰኛ ምክር ቤት አባል ማይክ ኮፍማን በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ በተዘጋጀው ውሳኔ ላይ የአገራቸው ምክር ቤት ድምፅ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:24

የማይክ ኮፍማን ጥሪ

ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ የሚተቸው እና HR 128 የተባለው ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ድምፅ ይሰጥበታል የተባለው ባለፈው ወር ነበር። የውሳኔ ሐሳቡ ደጋፊዎች እንደሚሉት ረቂቁ ድምፅ ሳይሰጥበት የቀረው የኢትዮጵያ መንግሥት ባሳደረው ጫና ምክንያት ነው። HR 128 ላይ ድምፅ ከሰጠን የኢትዮጵያ መንግሥት ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያለውን የጸጥታ ሥምምነት አቋርጣለሁ ብሏል ሲሉ ማይክ ኮፍማን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ችግሩን ከመፍታት እና ዴሞክራሲያዊ አገር ከመመስረት ይልቅ በወር 150,000 ዶላር እየከፈለ የውሳኔ ሐሳቡ ድምፅ እንዳይሰጥበት የሚወተውት ድርጅት ቀጥሯል ሲሉ ማይክ ኮፍማን ወቅሰዋል። ሒውማን ራይትስ ዎች ሌሎች  የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ቀደም ብለው ረቂቅ የውሳኔ ሐሳቡ ላይ ድምፅ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለአሜሪካ የታችኛው ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ፖል ሪያን ፅፈው ነበር። 
መክብብ ሸዋ
እሸቴበቀለ
ሸዋዬ ለገሠ
 

Audios and videos on the topic