የኢትዮጵያን ወጣቶች የሚፈታተነው ስራ አጥነት የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ርዕስ ነው። ጥቂት ወጣቶች ተሞክሮዋቸውን ይገልፁልናል።
የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳችን ከጫማ ጠራጊነት ተነስቶ፣ የንግድ ሱቅ ከፍቶ ራሱን ለመቻል በመፍጨርጨር ላይ እያለ፤ በተተመነበት የቀን ገቢ ግብር ምክንያት ሱቁን ዘግቶ ለመቀመጥ የተገደደ የ 25 ዓመት ወጣት ነው።
የምሥራቅ አፍሪቃ ሕዝብ በዓመት በ3% እያደገ ነው። እአአ 2100 በአፍሪቃ አራት ቢልዮን ሰው እንደሚኖር ግምቶች ያሳያሉ። ዓ/አቀፉ የገንዘብ መርህ ድርጅት እንደሚለው፣ በቂ የስራ ቦታ፣ ምግብና ማህበራዊ አገልግሎት እስካለ ድረስ ወጣቱ ፈጣን የኤኮኖሚ እድገት ለማስገኘት ጥሩ እድል ይፈጥራል። ይሁንና፣ የስራ ቦታን በተመለከተ ትልቅ ችግር ይታያል።
የወጣቶችን የስራ ዕድል ፈጠራ ለማበረታታት፣ ማለትም፣ ወጣቶች በቀላሉ ብድር ማግኘት የሚችሉበትን 10 ቢሊየን ብር የያዘ የወጣቶች የዕድገትና ልማት ተዘዋዋሪ ገንዘብ ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርጓል። የዚሁ አዲስ እቅድ አፈጻጸም ሂደት እንዴትነት እና በገሀድ የሚኖረው ትርጓሜ ምን ይመስላል?