የኢራን የኑክሌር ተቋምና ዉዝግቡ | ዓለም | DW | 18.08.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የኢራን የኑክሌር ተቋምና ዉዝግቡ

የቡሻሒሩ ማምንጫ ጣቢያ ግንባታ መጠናቀቁ እንደተሰማ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣን እስራኤል የኑክ’ሌር ጣቢያዉን በቦምብ ትመታዋለች በማለት አስፈራርተዋል።

default

የቡሻሒር የኑክሌር ተቋም

ኢራን በምዕራባዊቷ የወደብ ከተማዋ ቡሻሒር ያስገነባችዉ የኑክሌር ሐይል ማምንጫ ጣቢያ በመጪዉ ሳምንት በይፋ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።በሩሲያ ባለሙያዎች ድጋፍ የተገነባዉ የኑክሌር ጣቢያ ሥራዉን የሚጀምረዉ «ኢራን የኑክሌር ቦምብ ለማምረት ታደባለች የሚለዉ የዩናይትድ ስቴትስና የተባባሪዎችዋ ዉንጀላ ባየለበት ወቅት መሆኑ ነዉ።» የቡሻሒሩ ማምንጫ ጣቢያ ግንባታ መጠናቀቁ እንደተሰማ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣን እስራኤል የኑክ’ሌር ጣቢያዉን በቦምብ ትመታዋለች በማለት አስፈራርተዋል።የኢራን ባለሥልጣናት ግን እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ ተቋሞን ለመምታት ከቃጡ መዘዙ ቀላል እንደማይሆን እያስጠነቀቁ ነዉ።የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ነብዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች