1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የኢራን እና የምዕራቡ ድርድር

ቱርክ ኢስታንቡል ዉስጥ በአወዛጋቢዉ የኢራን የአቶም መረሃ-ግብር የተደረገዉ ዉይይት ትንሽም ቢሆን ተስፋ ሰጭ መሆኑ ነዉ የተገለጸዉ። በሌላ በኩል ዩኤስ አሜሪካ የኢራንን መንግስት ተቃዋሚዎች በስለላ በማሰልጠን ላይ መሆንዋ ተጋልጦአል።

ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ ቱርክ ኢስታንቡል ዉስጥ በአወዛጋቢዉ የኢራን የአቶም መረሃ-ግብር የተደረገዉ ዉይይት ትንሽም ቢሆን ተስፋ ሰጭ መሆኑ ነዉ የተገለጸዉ። በሌላ በኩል ዩኤስ አሜሪካ የኢራንን መንግስት ተቃዋሚዎች በስለላና ጥበብ በማሰልጠን ላይ መሆንዋ ተጋልጦአል። ስልጠናዉ የኢራንን የአቶም መረሃ-ግብር እቅድ ለመቋቋም የግድ አስፈላጊ መሆኑ እንደሚታመንበትም ተገልጾአል።

የኢራን መንግስት ተቃዋሚዎች በሚኖሩበት በቀድሞዉ የአሜሪካ የአቶም ሃይል መሳርያ መሞከርያ በነበረዉ በኒቫዳ በረሃ ልክ በአገራቸዉ በኢራን እንደሚኖሩ ሁሉ ሊያስቡት ይችላሉ። የኒቫዳ በረሃ የመልከ አምድር አቀማመጥ ከሰሜናዊ ምዕራብ ኢራን አካባቢ ገጽታ ጋር ተመሳሳይነት አለዉ። ይህ ድፍን ያለ እና የተከለለ ቦታ በአሜሪካ የሃይል ሚኒስቴር ኋላፊነት ስር ሲሆን ከሎሳንጀለስ ከተማ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። በዩኤስ አሜሪካ በሃይል ምንጭ ሚኒስቴር ስር የታጠረዉ ክልል በሎሳንጀለስ ከተማ የራሱ የሆነ የአየር ማረፍያ ያለዉ ሲሆን ለስለላ ጥበብ ስልጠና ተማሪዎችን በግል አዉሮፕላን ወደ በረሃዉ ይመላለሳሉ። እንደዉነቱ ከሆነ ይላል የአሜሪካ የሚሊተር ጉዳይ ተመራማሪ ጋዜጠኛ ሳይሙር ሄርሽ ፣ ይሄ የተከለለ ስፍራ ለአሜሪካ ወሳኝነት ያለዉ የመከላከያ ሚኒስቴር ነዉ። በኒቫዳ በረሃ በሚገኘዉ በዚህ ጥብቅ ቦታ አንድ ልዩ የአሜሪካ ኮማንዶ ጦር ለአመታት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ የኢራን መንግስት ተቃዋሚ ቡድናትን በስለላ ጥበብ አሰልጥነዋል። ከፕሪዝደንት ጆርጅ ቡሽ ዳግማዊ በፊት የነበሩ የዩኤስ አሜሪካ መሪዎች ግን ይህን ቡድን አልተቀበሉትም «የፋርሱንጉሰ መንግስት ከተወገደ ወዲህ ጀምሮሜክከኢራኑሙላህአስተዳደርጋርየጦርነትያህልሁኔታላይይገኛል።»

ሜክየተሰኘዉአህጽሮትሙጃሂዲንኢ ኸላቅ ላክየሙጃሂዲንህዝብእንደማለትነዉ።በ70 ዎቹ አመታት በኢራን ተማሪዎች የተመሰረተዉ ይህ ቡድን ስድስት አሜሪካዉያን ዜጎች በተገደሉበት ሲራ ላይ እጁ ያለበት ሲሆን የዮናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቡድኑን በጎ,አ 1997 አም አንድ የዉጭ የአሸባሪ ቡድን ሲል ፈርጆታል። እንድያም ሆኖ የጆርጅ ዳብሊ ቡሽን መንግስት የኢራኑን የሙጃሂዲንካላክወይም የኢራኑን የመንግስት ተቃዋሚ ቡድን በዩኢስ ልዩ ኮማንዶ በኒቫዳ በረሃ ካለማሰልጠን አልተገታም፣ ስልጠናዉም ልዩ የስለላ ጥብብን የያዘ ነዉ ይላል የጦር ሃይል ጉዳይ ምሁሩ ሳይሙር ኸርሽ

«እኛ፣ ማለት አሜሪካዉያን እነዚህን የኢራን መንግስት ተቃዋሚዎች ልዩ የስለላ ጥበብ ስልጠና እያሳወቅናቸዉ ነዉ »

በኒቫዳ በአሜሪካን ጦር እገዛ ይሰለጥን የነበረዉ አሸባሪ የሚባለዉ የኢራን ቡድን ኦባማ ስልጣን ላይ ከወጡ ጀምሮ ቆሞአል። ግን እንደ ሰይሙር ኸርሽ ክትትል እና ገለጻ የዩኤስ ወታደራዊ ስለላ ድርጅት እና የዩኤስ የዉጭ የስለላ ድርጅት CIA፣ በኒቫዳ በረሃ ላይ ከሰለጠኑት እና በአገራቸዉ እየሰሩ ካሉት የኢራን ህዝባዊ ሙጃኢዲን ጋር በጥምረት ይሰራሉ።

በሌላ በኩል ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ ቱርክ-ኢስታምቡል ውስጥ የተካሄደዉ የኢራን አቶም ንግግር በጥቂቱም ቢሆን ተሥፋ ሰጭ መሆኑ ተነግሮለታአል። ከተካሄደዉ የመጀመርያ ዉይይት በኋላ የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ፖሊሲ ተጠሪ ካትሪን አሽተን፣ ጥንቃቄ በተሞላበት የሁኔታ የንግሩን አዎንታነት አሳይተዋል።

«እንደማስበዉ ከመጀመርያዉ ግልጽ እንዳደረግነዉ አላማችን ይህን ሂደት አንድ እርምጃ ወደፍት ለመግፋት ነዉ። እናም የዉጤቱን መመዘኛዎች መጻፍ ብቻ ሳይሆን፣ መጭዉ ዉይይት የሚደረግብትን ቦታና ቀን ማሳወቅም ነዉ »

ቀጣዩ የአቶም ጉዳይ ዉዝግብ ንግግር ግንቦት 23 ባግዳድ ላይ እንደሚደረግም አሽተን ገልጸዋል። ዓለምአቀፉ ማሕበረሰብ የኢራንን የአቶም ፕሮግራም ለማስቆም አዲስ ሙከራ ሲያደርግ የአሁኑ ከ 15 ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው። በኢስታምቡሉ ስብሰባ የተቀመጡት የኢራን የአቶም ተደራዳሪ ሣኢድ ጃላሊ፤ እንዲሁም 5ቱ የጸጥታው ም/ቤት ቋሚ ዓባል መንግሥታትና የጀርመን ተጠሪዎች ነበሩ።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ