የኢሕአዴግ ሃያኛ ዓመትና የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ | ኤኮኖሚ | DW | 25.05.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የኢሕአዴግ ሃያኛ ዓመትና የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ

ኢትዮጵያ ውስጥ የወቅቱ ገዢ ፓርቲ እሕአዴግ ሥልጣን ከያዘ ይሄው ሰሞኑን ሃያ ዓመቱን ሊደፍን ነው። በዚሁ ጊዜ ውስጥ ደግሞ የአገሪቱ የኤኮኖሚ ዕድገት ዓቢይ መነጋገሪያ ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል።

default

ያለፉት ሃያ ዓመታት በኢትዮጵያ የነጎዱት ተሥፋና ስጋት የተዋሃዳቸው ሆነው ነው። የሕዝቡ ተሥፋ በአንድ በኩል በተለይም በኤኮኖሚ ዕድገት የሚያሳዝን ሆኖ የአገሪቱ መለያ ከሆነው ከድህነትና ከረሃብ መላቀቅ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም የኢትዮጵያ ሕዝብ በቀን ሶሥቴ በመመገብ ጠግቦ ለማደር እንዲበቃ በጊዜው መመኘት ማለማቸው አልቀረም። ይህ ሁሉ ተሥፋ ዛሬ ከምን ደረሰ፤ በኢትዮጵያ የፊናንስና ልማት ሚኒስቴር የግንኙነት ሃላፊ አቶ ሃጂ ኢብሣ በበኩላቸው መንግሥት ቀደም ባሉት አስተዳደሮች አቻ ያልታየለት ዕድገት ማስመዝገቡን ነው የሚናገሩት።
ሌሎች ግን ለየት ያለ አስተያየት አላቸው። ለምሳሌ ያህል የቀድሞው የም/ቤት ዓባል አቶ ተመስገን ዘውዴ፣ በወቅቱ ብቸኛው የም/ቤት ዓባል አቶ ግርማ ሰይፉም ዕድገቱን አንጻራዊ አድርገው ተመልክተውታል። ፕሮፌሰር ማሞ ሙጬ ደግሞ በተቀዳሚ የሕብረተብ ዕድገት ዕውን እንዲሆን የመንግሥቱ የኤኮኖሚ ፖሊሲ ሊስተካከል ይገል ባይ ናቸው።

መረጃዎችን ለመጠቃቀስ ኢትዮጵያ ዛሬም የፖለቲካ ለውጥ ከተደረገ ከሃያ ዓመታት በኋላም በዓለም ላይ በዝቅተኛ የልማት ደረጃ ላይ የሚገኙ ሊትስ-ዴቨሎፕድ ተብለው ከተደለደሉት የድሃ ድሃ ተብዬ አገሮች አንዷ ናት። በቅርብ በወጣ የሰብዓዊ ወይም ማሕበራዊ ዕድገት መረጃ ዝርዝር መሠረት ኢትዮጵያ ከ 178 አገሮች 171ኛዋ ሆና ነው የምትገኘው። በሌላ በኩል መንግሥት እንደሚለው ባለፉት ዓመታት በተከታታይ ከፍተኛ የኤኮኖሚ ዕድገት ታይቷል። ከሆነ ለምንድነው የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ያልተቻለው? በሕዝብ የኑሮ ሁኔታ መሻሻል ውይም ማሕበራዊ ዕድገት ሲንጸባረቅስ የማይታየው? ይህ የመጪዎቹ ዓመታት ዓቢይ የልማት ውይይት ርዕስ የሚሆን ነው የሚመስለው።

መሥፍን መኮንን

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች