1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአፍሪቃ መሪዎች ዉሳኔና የሕብረቱ ሥልጣን

የዉሳኔዉ ዝር ዝር እንደሚያመለክተዉ የአፍሪቃ ባለሥልጣን አባል ሐገራትን የሚወክለዉ የንግድን በተመለከተ በሚደረጉ ድርድሮች እንጂ በመከላከያ አይደለም።

default

የሲርቱ ጉባኤ

030609

የአፍሪቃ ሕብረት አባል ሐገራት የመሪዎች ጉባኤ የሕብረቱን ሥልጣንና ሐላፊነት ለማጠናቀር የተረቀቀዉን እቅድ አፀደቀ።ሲርት-ሊቢያ የተሰበሰቡት የአባል ሐገራት መሪዎች ትናንት ለዛሬ አጥቢያ ባሰለፉት ዉሳኔ መሠረት ሕብረቱ የአባል ሐገራትን የመከላከያና የንግድ መርሕን ያቀናጀል። ከመሪዎቹ ጉባኤ ጎን ለጎን የተሰየመዉ የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ሥብሰባ ደግሞ ሕብረቱ ከአለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ጋር እንዳይተባበር ወስነዋል።በላይፕዚሽ ዩኒቨርስቲ የአፍሪቃ ጥናት ፕሮፌሰር ኡልፍ ኤንግል እንደሚሉት የመሪዎቹም የሚኒስትሮቹ ዉሳኔ አጠያያቂ ጉዳዮችን ማስነሳቱ አይቀርም።

የአፍሪቃ ሕብረት ወደ ተባበረዉ የአፍሪቃ መንግሥታትነት ማደግ አለበት በሚሉት ሊቢያንና ተባባሪዎቻቸዉን በመሳሰሉት ሐገራትና ሐሳቡን በሚቃወሙት እንደ ደቡብ አፍሪቃ፥ ናጀሪያ ባሉ ሐገራት መካካል የሚካሔደዉ ሽኩቻ፥ ሙግት፥ክርክር ትናንትም ጎሕ እስኪቀድ እንደጋጋመ ነበር።

ዛሬ ከመብረቁ በፊት ግን ሙግት ክርክር ደርዝ መያዙ ቢያንስ ላሁኑ ለሁለቱ ወገኖች እፎይታ-ፋታ መሆኑ አልቀረም።መሪዎቹ በደረሰቡት ስምምነት መሠረት ከዚሕ ቀደም እንዲመሰረት የተወሰነዉ የአፍሪቃ ባለሥልጣን የአባል ሐገራትን የመከላከያ መርሕ ያቀናጃል።በአለም አቀፍ የንግድ ድርድሮች አባል ሐገራትን ይወክላል።አንዳድ ታዛቢዎች እንደሚሉት ዉሳኔዉ የተባበሩት የአፍሪቃ መንግሥታትን ለመመስረት መንገድ ጠራጊ፥ የዚሕ ሐሳብ አራማጆችን ለሚያስተባብሩትና ለጉባኤዉ አስተናጋጅ ለሊቢያዉ መሪ ለሙአመር ቃዛፊ ታላቅ ድል ነዉ።

በላይፕዚሽ-ጀርመን ዩኒቨርስቲ የአፍሪቃ ጥናንት ተቋም ፕሬፌሰር ኡልፍ ኤንግል ግን እዉነታዉ ተቃራዊዉ ነዉ-ባይ ናቸዉ።

«እስካሁን ድረስ እንደዚያ አይደለም።የትናንት ሌሊቱ የመግባቢያ ሐሳብ ገና ያልፀደቀ ዉሳኔ ነዉ።መሪዎቹ ከዉሳኔዉ ጎን ለጎን የአፍሪቃ ሕብረት ሥራ-አስፈፃሚ ማለት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ምክር ቤት ጉዳይ በቅጡ እንዲመረምረዉም ወስነዋል።ይሕ የሆነበትም ምክንያት የተባበሩት የአፍሪቃ መንግሥታት እንዲመሰረት የሚከራከሩት ሊቢያን የመሳሰሉት ሐገራት ከደቡብ አፍሪቃ፥ ከናጀሪያና ከብጤዎቻቸዉ ጠንካራ ተቃዉሞ በመቅረቡ ነበር።»

ያም ሆኖ ዉሳኔዉ ሕብረቱን ይበልጥ ለማጠናከር ከዚሕ ቀደም ለሚደረገዉ ጥረት ገቢራዊነት ሁነኛ መሠረት መጣሉን ፕሮፌሰር ኤንግል ይስማማሉ።

«በዉሳኔዉ ላይ ከዚሕ ቀደም ይታወቅ የነበረዉ የአፍሪቃ ሕብረት ፕሬዝዳና ምክትል ፕሬዝዳት ያለዉ፥ የእስካሁኑ ኮሚሽን በፀሐፊነት የሚያገለግሉበት የአፍሪቃ ባለሥልጣን እንዲሆን ተጠቅሷል።»

ዛሬ ጧት ስምምነቱ እንደተሰማ-የአፍሪቃ ሐገራት የጋራ መከላከያ ሊኖራቸዉ የሚል አይነት ትርጓሜ ተሰጥቶት ነበር።ይሁንና የዉሳኔዉ ዝር ዝር እንደሚያመለክተዉ የአፍሪቃ ባለሥልጣን አባል ሐገራትን የሚወክለዉ የንግድን በተመለከተ በሚደረጉ ድርድሮች እንጂ በመከላከያ አይደለም።እንደገና ፕሮፌሰር ኤንግል።

«አዲሱ ነገር በንግድ ጉዳዮች ላይ በሚደረጉ አለም አቀፍ ድርድሮች የአፍሪቃ ባለሥልጣን አባል ሐገራትን ወክሎ እንዲደራደር ሥልጣን ማግኘቱ ነዉ።ይሕ ተረቅቋል።»ዉክልናዉ በንግድ እንጂ በመከላከያ ጉዳይ አይደለም።ይሕ ማለት በመከላከያ ረገድ ወትሮም የሚያግባቡት ተቋማት ተቀናጅተዉ ይሠራሉ ማለት ነዉ።»

መሪዎቹ የአፍሪቃ ሕብረትን ሥልጣንና ሐላፊነት ለማጠናከር ተስማምተዋል።ይሕ ስምምነት- የተባበሩት የአፍሪቃ መንግሥታት ይመስረት ከሚሉትም፥ ይሕን ከሚቃወሙትም መሐል መንገድ ላይ ያለ ይመስላል።የዉሳኔዉ ይዘት ሁለቱን ወገኖች የሚያግባባ ነዉ- ባዮችም አልጠፉም።ፕሮፌሰር ኤግል በዚሕ አይስማሙም።

«እኔ እንደማቀራረቢያ አድርጌ አልወስደዉም።ይሕ አብዛኞቹ ሐገራት በጋዳፊ አንፃር መቆማቸዉን የሚያሳይ ዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ነዉ።ክርክር ያልተደረገበት ጉዳይ ግን አለ።ይህም በጋዳፊና በሌሎቹ አፍሪቃዉያን መካካል ሳይሆን፥ በሌሎቹ አፍሪቃዉያን በራሳቸዉ መካካል የአፍሪቃ ሕብረት ለማጠናከር አስተዳደራዊ ማለት ቴክኒካዊ መፍትሔ ይፈለግ በሚሉትና እና የአዉሮጳ ኮሚሽንን ያክል ርቀት መሔድ የሌለበት ግን ሰፋ ያለ የሉአላዊነት አጥር ያለዉ መሆን አለበት በሚሉት መካካል።»

አለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳጃ ፍርድ ቤት የሱዳኑ ፕሬዝዳት ዑመር ሐሰን አልበሽር እንዲያታሰሩ ከወሰነ ጊዜ ጀምሮ የአፍሪቃ ሐገራት ዉሳኔዉን አጥብቀዉ እንደተቋወሙት ነዉ።ዛሬ ደግሞ የአባል ሐገራት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ከፍርድ ቤቱ ጋር ላለመተባበር ወስነዋል።የዉሳኔዉ ገቢራዊነት ግን አጠያያቂ ነዉ-እንደ ፕሮፌሰሩ
«የዉሳኔዉ ረቂቅ ከአለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ጋር መተባበር አንፈልግም የሚል ነዉ።ለዚሕ ምክንያቱ የአፍሪቃ ሕብረት የሚያደርገዉ ድርድር ላደጋ በመጋለጡ ነዉ።ይሕ አንድ ነገር ይጠቁማል።ከሰላሳ የሚበልጡ አባል ሐገራት የገቡትን አለም አቀፍ ግዴታ ይጎደዋል።ገቢራዊነቱ እንዴት እንደሆነ ወደፊት የሚታይ ነዉ።»

ቃለ-ምልልስ፣ ከዑልፍ ኤንግል ጋር--

ነጋሽ መሐመድ፣

ተክሌ የኋላ፣

ተዛማጅ ዘገባዎች