የአፍሪቃ ህብረት የመከላከያ ሚንስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ ተጀምሮዋል።
በህብረቱ የስብሰባ አዳራሽ የተጀመረውን ስብሰባ የከፈቱት የአፍሪቃ ህብረት የጸጥታና የደህንነት ምክር ቤት ኮሚሽነር ራምታን ላማምራ ናቸው። ስብሰባው በህብረቱ ሰላም አስከባሪ ተልዕኮዎች አወቃቀር ላይ በተይ ያተኮረ ሲሆን፡ የኮት ዲቯርን ጊዚያዊ ሁኔታም ተወያይቶበታል።
ታደሰ እንግዳው
አርያም ተክሌ ነጋሽ መሀመድ
በኢትዮጵያ ያሉ ስጋ ቤቶች ከሚታወቁበት የልኳንዳ ብቻ አገልግሎት ተላቅቀው እንደ ምግብ ቤት ማገልገል ከጀመሩ ቆይተዋል፡፡ ከዘመኑ ጋር ለመራመድ ጥረት የሚያደርጉ ስጋ ቤቶች ደግሞ ስማቸው ከሚጠራ የመዝናኛ ስፍራዎች መካከል ራሳቸውን ማሰለፍ ችለዋል፡፡ ጥቂቶቹ መሰረታቸውን ከጣሉበት ከተማ ተሻግረው በአዲስ አበባ ቅርንጫፎች እስከ መክፈት ተጉዘዋል፡፡
እስረኞቹ መጨረሻ የተለቀቁትም ሕዝብ ባደረገዉ ተከታታይ ተቃዉሞ፤ የአደባባይ ሠልፍ እና አድማ መሆኑ አላጠያየቅም።የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች እራሳቸዉን፤ ባልደረቦቻቸዉን ወይም ተከታዮቻቸዉን በደለ እያሉ የሚያወግዙት መንግሥት ለወደፊቱ ተመሳሳይ በደል ላለመፈፀሙ ምን ዋስትና አግኘተዉ ነዉ አዲሱ መሪ በጠሩት ግብዣ ላይ የተካፈሉት?
ዛሬ በተካሄደው የለንደን ማራቶን ውድድር በወንዶች ቶላ ሹራ ሁለተኛ ሲወጣ በሴቶች ደግሞ ታደለች በቀለ ሶስተኛ ሆናለች። ውድድሩን ያሸንፋሉ በሚል ሲጠበቁ የነበሩት ኢትዮጵያውያኑ ቀነኒሳ በቀለ እና ጥሩነሽ ዲባባ አልቀናቸውም፡፡ ቀነኒሳ ውድድሩን በስድስተኛነት ሲያጠናቅቅ ጥሩነሽ ውድድሩን አቋርጣ ወጥታለች፡፡