የአፍሪቃና የዩኤስ አሜሪካ የንግድ ትብብር | ኤኮኖሚ | DW | 04.08.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የአፍሪቃና የዩኤስ አሜሪካ የንግድ ትብብር

ዩኤስ አሜሪካና አፍሪቃ «አፍሪካን ጎውዝ ኤንድ ኦፖርቹኒቲ አክት» በአሕጽሮት «አጎዋ» በሚል ውል የንግድና የኤኮኖሚ ትብብር እንደሚያደርጉ የሚታወቅ ጉዳይ ነው።

default

የአሜሪካ መንግሥት ፍቱን በሆነ የልማት ዕርዳታና መዋዕለ-ነዋይ አቅርቦት ዕድገትን ለማራመድ የሚሻ ሲሆን ነገር ግን በተለይም ሙስናና ደካማ መዋቅራዊ ይዞታ የታሰበው ዕርምጃ እንዳይደረግ እንቅፋት ሆኗል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪይ ክሊንተን 12 በመቶው የዓለም ሕዝብ የሚኖርባት አፍሪቃ ከዓለምአቀፉ ምርት ከሁለት ከመቶ እንዳላለፈች በመጥቀስ ለውጥ ማስፈለጉን ነው ያመለከቱት።

በአሜሪካና በአፍሪቃ የንግድና የኤኮኖሚ ትብብር ረገድ የሙስናና የንግድ መሰናክሎች ችግር ሲነሣ አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪይ ክሊንተን የዛሬ ዓመት በአፍሪቃ ጉብኝታቸው ለማንኛውም ዕርምጃ በጎ አስተዳደር ወሣኝ መሆኑን ነበር ያስገነዘቡት።

“የግንኙነቱ ዕርምጃ በበጎ አስተዳደርና በሕግ የበላይነት መከበር ላይ ጥገኛ ነው። ይህ ጥሩና አስተማማኝ ለሆነ የመዋዕለ-ነዋይ ሁኔታ መፈጠር ወሣኝነት ይኖረዋል። በሃገራትና በወሰኖች መካከል አንዳንዴ በቀላሉ የማይገፉ ችግሮች እንዳሉ አወቃለሁ። ግን በነዚህ ላይ ማተኮሩ የኦዋ ግዴታ ነው”

ቀጠል አድርገውም፤

“አሁን ዩናይትድ ስቴትስም ሃላፊነቶች አሉባት። የንግድ አቅምን ለማዳበር በመላው አፍሪቃ የተያዙ ጥረቶችን እናጠናክራለን” ነበር ያሉት።

ይህ መንፈስ ዛሬም አልተለወጠም። ውሉ በፊታችን ሲያከትም እንደገና የሚራዘም መሆኑ ነው የሚጠበቀው። ይሁንና በሌላ በኩል የኤኮኖሚው ባለሙያ አቶ እንዳክላቸው ተሥፋዬ እንደሚሉት ወደፊት ስኬት ለማግኘት የአፍሪቃ መሪዎች በተለይም ሙስናን በመታገሉ ረገድ በጣሙን መጣራቸው ግድ ነው። ያድምጡ!

መሥፍን መኮንን

አርያም ተክሌ