የአዲስ አመት ልዩ ዝግጅት | ኢትዮጵያ | DW | 11.09.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአዲስ አመት ልዩ ዝግጅት

የተራድኦ ድርጅቶች ሕግ፥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ደንብ፥ የፀረ-ሽብርተኞች ሕግ ሌላም አያሌ ሕግጋት ፀድቀዋባታል።አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፥ የፕረስ ነፃነት ተከራካሪዎች፥ የግብረሰናይ ድርጅቶችና አብዛኞቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሕግ ደንቦቹን ተቃዉመዋቸዋል።

default

ጊዜ-በጊዜ ቀለበት ሰተት-እንዳለዉ ገጣሚዉ ሆኖ፥ ዛሬና ከዛሬ በሕዋላ እስከ መጪዉ አመት-የዛሬን ዕለት ድረስ አምና የምንለዉ አመት በዘንዶሮ-ባልነዉ ቀለበት እስኪገባ ሕይወት በግልም፥ በማሕበርም፥ በሐገርም ደረጃ ብዙ ጓጥ-ስርጓጉጥ፥ ፌስታ ደስታንም መዘናገር ነበረባት።
እንደ ሐገር-ዛሬ የአዲስ አመአቷን ሰወስተኛ አመት-አንድ ያላቸዉ ኢትዮጵያ አምና ከደግ-ደጉ ይልቅ ክፋት፥ ሸሩ ጠንቶባት መክረሙ ነዉ-ሰቀቀኑ።

የተራድኦ ድርጅቶች ሕግ፥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ደንብ፥ የፀረ-ሽብርተኞች ሕግ ሌላም አያሌ ሕግጋት ፀድቀዋባታል።አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፥ የፕረስ ነፃነት ተከራካሪዎች፥ የግብረሰናይ ድርጅቶችና አብዛኞቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሕግ ደንቦቹን ተቃዉመዋቸዋል።

ሕግ-ደንቦቹ አሟግተዉ ሳበቁ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ሴት የፖለቲካ ፓርቲ መሪ-ወሕኒ ወረዱ።ወይዘሪት-ብሩቱካን ሚዴ ቅሳ።ዘንድሮ-የምርጫ አመት ነዉ።ካምና ይሻል-ይሆን።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን የታደሰ እንግዳዉ ዘገባ መልስ ከሆኑ-ከአዎዉ ይልቅ-አዩ ነዉ-የሚያይል።
ከሰባ-እስከ መቶ ሺሕ የሚገመት ወጣት የረገፈበት የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ዉዝግብ ሁለት-ሺሕ አንድንም እንደ ቀዳሚዎቹ አስራ-አንድ አመታት በዉጥረት-ሥጋት ተቀበሎ-ሸኘዉ።

የለም አቀፉ የካሳ ኮሚሽን አምና-በወሰነዉ መሠረት ኢትዮጵያ ከወጪ ቀሪ አስር ሚሊዮን ዶላር ያሕል ከኤርትራ ትካሳለች።ወደብ ላይ ሐብት ንብረታቸዉ የጠፋባቸዉ ኢትዮጵያዉያን ነጋዴዎች ግን እንደከሰርን ቀረን-እንዳሉ-ሁለት ሺሕ-አንድ አምና ሆነ።ከባድመ አልፎ-መቅዲሾ የደረሰዉ የኢትዮጵያ ኤርትራ ጠብም ሶማሊያ የዶለዉ የኢትዮጵያ ወደ ሐገሩ የተመሰዉ አምና ነዉ።ጥር።

ጦሩ ሶማሊያን ለቅቆ የወጣዉ እንደ ኢትዮጵያ መንግሥት በግለጫ በድል አድራጊነት፥ እንደ ሶማሊያ ደፈጣ ተዋጊዎች አባባል ደግሞ ሽንፈት ተከናንቦ-ነዉ።ጦሩ ድል-ነሳም ተነሳ ዘመቻዉ ለሶማሊያ ሰላም የፈየደዉ የለም።ጎይቶም ቢሆን ከአስመራ እንደዘገበዉ ኤርትራዉያንም ልክ እንደ ኢትዮጵያ ልክ እንደ ሶማሊያ ሕዝብ ፀሎት ምኞታቸዉ ሰላም ነዉ።

Blumen Geschenk

መልካም አዲስ ዓመት

የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለሚካኤል ካነጋገራቸዉ በርካታ ኢትዮጵያዉን ቢያንስ ሁለቱ-በየፊናቸዉ ያነሱት አንድ የጋራ ነገር-አለ።የሐይማኖት ግጭት።ለዘመናት የሐይማኖቶች መቻቻል አብነት ተነደርጋ የምትታየዉ ኢትዮጵያ እንደ ብዙ ገፅታዎችዋ-ይሕንንም ከነበር ሰንዱቋ እንዳትቆልፍበት በርግጥ ሊያሰጋ ይገባል።የአስተያየት ሰጪዎቹ ምኞት-ተስፋ መቻቻሉ በግጭት፥መተሳሰቡ በእብጠት ትዕቢት እንዳይቀየር የሚል-ነዉ።

ከ1994 ወዲሕ የኢትዮጵያዉያኑ የመልካም-ምኞት፥ በጎ ተስፋ መሰነቂያዋ ዕለት ለአሜሪካኖች የመጥፎ ድርጊት ትዉሳታ መቀስቀሻ ናት።ናይን-ኢለቨን እንደነሱ። ዛሬ ስምንተኛ አመቱ። አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ግን የዋሽግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ እንደዘገበዉ ቢያንስ ለዘመን መለወጫ ሮም-ስትኖር እንደሮሞች ሁን ብሎ ብሒልን አይቀበሉትም።

Negash Mohammed


Audios and videos on the topic